"የተባበሩት አረብ ኤምሬት ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እየተሰራ ነው" - አምባሳደር አክሊሉ ከበደ
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንስል ጄኔራል ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ ገለፁ።
አምባሳደሩ ይህን የገለፁት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ከተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ፤ የኮርፖሬት ሀብት ማኔጅመንት ዘርፍ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ሰይፉ እና የኢንቨስትመንት ዘርፍ አማካሪ ወ/ሮ ማህሌት ሽባባው የተመራ ልዑክ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኙ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከአምባሳደሩ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲን በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ስለሚገኙ የኢንቨስትመንት ፣ የንግድና የሎጂስቲክስ እድሎች ፤ አማራጮችና ማበረታቻዎች ዙሪያ እንዲሁም ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ስላደረጋቸው ኢንቨስተር ተኮር ሪፎርሞችና ፈጣን የአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ሰፊ ገለፃ በመድረኩ አቅርበዋል።
ክቡር አምባሳደር አክሊሉ ከበደ በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ኢንቨስተሮችን ለመሳብ በየአህጉሩ የተከፋፈለ ዴስክ በማዋቀር ጭምር እየተንቀሳቀሰ ያለበትና አሁን ላይ ለኢንቨስተሮች እየሰጠ ያለው ያልተቋረጠ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለኢንቨስትመንት ፍሰቱ ማደግ ጉልህ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀው ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስታውሰዋል።
ልዑካን ቡድኑ በቆይታዉ ዱባይን ጨምሮ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ከፍተኛ መዋለ ነዋይ በማፍሰስ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ከተሰማራው የአርማዳ ግሩፕ ባለቤትና የማኔጅመንት አባላት ጋር በኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለይም በሪልስቴት ዘርፍ እንዲሰማራ ለማድረግ የሚያስችል ዉይይት ማድረጉ ይታወቃል።
'The embassy is stepping up efforts to attract investors from the UAE to invest in Ethiopia's industrial parks' - Ambassador Aklilu Kebede
Consul General H.E Aklilu Kebede stated FDRE Dubai and Northern Emirates consulate are working hard for UAE investors to invest in Ethiopia's industrial parks and Diredawa Free Trade Zone.
The ambassador stated this during a discussion with a delegation led by senior officials of the Industrial Parks Development Corporation.
A delegation led by IPDC's Investment Promotion and Marketing Deputy CEO Zemen Junedin , Coporate Resource Management Deputy CEO Alemayehu Seifu and Investment Sector Advisor Mahlet Shibabaw held discussions with the ambassador regarding the possible conditions for investors from the United Arab Emirates to invest in Ethiopia's industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone.
IPDC deputy CEO Zemen junedin, presented and gave broad explanation on investment, business, logistics, fiscal and non fiscal incentives as well as the investor-oriented reforms and zero waiting time that the corporation has implemented.
Ambassador Aklilu Kebede on his part pointed out that IPDC's positive effort setting up a desk in every continent to attract investors and providing uninterrupted and efficient service to investors has a significant contribution to the growth of the investment flow and reminded that this should be strengthened.
The delegation during their stay, held discussions with the owner and management members of the Armada Group, which has invested in various areas of the world, including Dubai, to enable it to engage in industrial parks, especially in the real estate sector.