• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 1 week ago
  • 440 Views

ፕሮጀክት አገልግሎቱ ለፊንጫ ስኳር ፋብሪካ

ፕሮጀክት አገልግሎቱ ለፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የሰራውን ጥናት አጠናቆ አስረከበ 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለፊንጫ ስኳር ፋብሪካ የሰራውን የአዋጭነት ጥናት ሰነድ አጠናቆ በዛሬው እለት አስረክቧል። 

የጥናት ሰነዱን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ለፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሃይለ ማርያም በፕሮጀክት አገልግሎቱ ቢሮ በይፋ አስረክበዋል። 

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት አገልግሎቱ ባለፉት ወራት የሀገራችን ትልልቅ ስኳር ፋብሪካዎችን ችግሮች በመለየትና በቀጣይ ወደ ትርፋማነት እንዲገቡ የሚያስችሉ ግዙፍና ሰፋፊ ጥናቶች ሰርቶ በማስረከቡ መደሰታቸውን ገልፀው ለወደፊትም ከሌሎች ሀገራዊ ፋዳድ ካላቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች ጋር አብሮ ለመስራት ፕሮጀክት አገልግሎቱ ከምንግዜውም በበለጠ ዝግጅት ማድረጉን አረጋግጠዋል። 

የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መንግስቱ ሀይለ ማርያም በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የአዋጭነት ጥናቱን በአጭር ጊዜና በታቀደው መሰረት አጠናቆ በማስረከቡ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው የስኳር ፋብሪካው  በአጭር ጊዜ ወደ ስራ ገብቶ ትርፋማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርግና ውጤታማ እንዲሆን በአብሮነት እንዲሰራ እንፈልጋለን ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በሃገራችን የሚገኙ የ5 ግዙፍ ስኳር ፋብሪካዎች የአዋጭነት ጥናትን ለመስራት ውል በመፈፀም ወደ ስራ የገባ ሲሆን የከሰም ፤ ጣና በለስና የፊንጫ ስኳር ፋብሪካዎችን የጥናት ሰነድ አጠናቆ ያስረከበ ሲሆን  የቀሪዎቹን የሁለቱን ደግሞ በአጭር ግዜ ለማጠናቀቅ እየሰራ እንደሚገኝ በርክክቡ ወቅት ተጠቁሟል።

Industrial Parks Development Corporation's Industrial Projects Service (IPS) has completed and submitted the feasibility study document for Fincha Sugar Factory. 

Shiferaw Solomon, General Manager of Industrial Projects Service, officially handover the document to Mengistu Hailemariam, General Manager of Fincha Sugar Factory today. 

During the handover ceremony, IPS General Manager M.r Shiferaw stated that the project service was happy to identify the problems of the country’s huge sugar factories in the past months and conduct a study that will enable them to become profitable. 

Mengistu Hailemariam, the General Manager of Fincha Sugar Factory, on his part, praised the Industrial Projects Service for completing the feasibility study in a short period of time as planned, and called  the project service to provide all the necessary support to make the sugar factory more profitable and operational in a short time. 

IPDC's Industrial Projects Service has entered into a contract to carry out a feasibility study of 5 huge sugar factories, and has completed and handed over the study documents for the Kesem, Tana beles and Fincha sugar factories, and is in the process of handing over the remaining two.