• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 1 week ago
  • 414 Views

የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ

የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የምርት ሂደት አበረታች መሆኑ ተገለፀ 

የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የምርት ሂደትና አጠቃላይ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ ገለፁ። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ ሂደት በተመለከቱበት ወቅት ነው። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል። 

ዶ/ር ፍሰሀ በዛሬው እለት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በነበራቸው ቆይታ በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ ኢንቨስተሮችና ኩባንያዎች ያሉበትን ወቅታዊ የምርት ሂደት ተዟዙረው ተመልክተዋል። በምልከታቸውም ጄፒ ቴክስታይል እና ሲልቨርስፓርክ የተሰኙ የሁለት አለም አቀፍ ኩባንያዎችን የምርት ሂደት ከመመልከታቸውም ባሻገር ከኩባንያዎቹ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። 

በዛሬው እለት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተደረገው የመስክ ምልከታ ጎን ለጎን የኢንዱስትሪ ፓርኩ ያለፉት 11 ወራት የስራ አፈፃፀም የሚገመገም ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርም እንደሚከናወን ይጠበቃል። 

Industrial Parks Development Corporation CEO, Dr. Fisseha Yitagesu stated that Hawasa Industrial Park's operation is encouraging. 

The CEO stated this while observing the current operational progress of Hawassa Industrial Park. 

The CEO with his management observed the current general activities of Hawasa Industrial Park today. 

During his stay at Hawassa Industrial Park today, Dr. Fisseha visited the current production process of manufacturing companies and investors in the park. In addition to observing the production process of two international companies named JP Textile and Silverspark, they discussed investment related issues with the top officials of the companies. 

Along with the field observation at Hawassa Industrial Park today, the performance of the industrial park for the past 11 months will be evaluated and it is expected that the green legacy program will be carried out.