• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 2 weeks ago
  • 431 Views

የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን በባለሀብቶች የመያዝ ምጣኔ ማሳደግ

"ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን ሙሉ ለሙሉ ማስያዝ ለነገ የምንተወው ጉዳይ አይደለም" - ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ 

ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን በአጭር ግዜ ሙሉ ለሙሉ በባለሀብቶች ማስያዝ እንደሚገባ እና ስራውም ለነገ የሚተው ጉዳይ እንዳልሆነ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ ገለፁ። 

ዶ/ር ፍሰሀ ይህን የገለፁት በዛሬው እለት የኢንዱስትሪ ፓርኩን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው በተመለከቱበት ወቅት ነው። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን አሁን ካለው በባለሀብቶች የመያዝ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግና በአለም አቀፍና በሀገር በቀል አምራች ኩባንያዎች ለማስያዝ ጠንካራ የፕሮሞሽን እና የማርኬቲንግ ስትራቴጂዎች ተቀርፀው በቅርቡ ተግባራዊ እንዲደረጉ እና በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ እንደ ሀገር የሚጠበቅበትን ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል። 

ዶ/ር ፍሰሀ በኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚገኙ የፋርማሲዩቲካል አምራች ኩባንያዎችን የምርት ሂደት በመመልከት ከኩባንያዎቹ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።  

በዛሬው የጉብኝት መርሀ ግብር በነበረው ቆይታ የፓርኩ የ2016 በጀት ዓመት የ11 ወራት የእቅድ አፈፃፀም ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን በቀጣይ 100 ቀናት በትኩረት መከናወን የሚገባቸው ዋና ዋና ግብ ተኮር ተግባራት ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል። 

'Kilinto Industrial Park should be occupied  completely by investors in a short period of time' - Dr. Fisseha Yitagesu 

Industrial Parks Development Corporation CEO Dr. Fisseha Yitagesu underlined that Kilinto Industrial Park should be occupied  completely by investors in a short period of time. 

Dr. Fisseha stated this today when he toured Kilinto industrial park's current operational activities. 

The CEO urged that strong promotion and marketing strategies should be designed and implemented soon to increase the rate of occupancy of Kilinto Industry Park by international and local manufacturing companies and tireless efforts should be done to to achieve the expected results in the pharmaceutical sector as a country. 

Dr. Fisseha observed the production process of the pharmaceutical manufacturing companies located in the industrial park and held a discussion with the managers of the companies. 

During today's tour schedule, the park's 11-month performance of 2016 fiscal year was presented and discussed, and the main goal-oriented activities that should be focused on in the next 100 days were set.