ፕሮጀክት አገልግሎቱ ለጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የሰራውን የጥናት ሰነድ አጠናቆ አስረከበ
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የአዋጭነት ጥናት ለመስራት ከተዋዋላቸው የስኳር ፋብሪካዎች መካከል 2ኛ የሆነውን የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የአዋጭነት ዝርዝር ጥናት ሰነድን አጠናቆ አስረክቧል።
የጥናት ሰነዱን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ለጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ይሁኔ በይፋ አስረክበዋል።
አቶ ሽፈራው በርክክቡ ወቅት እንደገለፁት ፕሮጀክት አገልግሎቱ የ5 ትልልቅ ስኳር ፋብሪካዎችን የአዋጭነት ጥናት ለመስራት ውል የፈጸመ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ባለፈው የ2ቱን ስኳር ፋብሪካዎች ጥናት አጠናቆ ማስረከቡን ገልፀው የ3ቱን ስኳር ፋብሪካዎች ጥናትም አጠናቆ ለማስረከብ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ይሁኔ የአዋጭነት ጥናቱ የስኳር ፋብሪካው በአጭር ጊዜ ወደ ስራ በመግባት ወደ ትርፋማነት እንዲሸጋገር የሚያግዝ መሆኑን በመግለፅ የአዋጭነት ጥናቱን በተቀመጠለት ጊዜ አጠናቆ ለማስረከብ ፕሮጀክት አገልግሎቱ ያደረገውን ያልተቋረጠ ድጋፍና ትብብር አድንቀዋል።
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት በጥናትና ማማከር ዘርፍ ፤ በአዋጭነት ጥናት ፤ በንብረት ትመና እና በተለያዩ የአገልገሎት ዘርፎች ከተለያዩ መንግስት ተቋማት ጋር ላለፉት 40 ዓመታት ሲሰራ የቆየ አንጋፋ ተቋም ሲሆን አሁንም የረጅም ዓመት ልምዱን ተጠቅሞ ከተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት አጋርነቱን በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡
Industrial Parks Development Corporation's Industrial Projects Service (IPS) has completed and submitted the feasibility study document for Tana Beles Sugar Factory.
Shiferaw Solomon, General Manager of Industrial Projects Service, officially handover the document to Abebe Yihune, General Manager of Tana Beles Sugar Factory.
During the handover ceremony, IPS General Manager Shiferaw stated that the project service has signed a contract to conduct feasibility studies for 5 huge sugar factories. He underlined that IPS already completed and submitted the studies for 2 sugar factories, and is now working to finish the studies for the remaining 3 factories.
Abebe Yehune, the General Manager of Tana Beles Sugar Factory, expressed that the feasibility study will help the factory become operational in a short period and become profitable.
IPDC's Industrial Projects Service has over 40 years of experience in research, consulting, and providing services to various government institutions in property management and other sectors. The project service continues to demonstrate its partnership by working with different institutions and organizations.