• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 3 months, 3 weeks ago
  • 185 Views

የክብርት ሚኒስትሯ መልዕክት

"የስራ እድል ፈጠራ እና የሰራተኞችን ክህሎት ማዳበር ላይ በጋራ መስራት ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው" ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚል 

የስራ እድል ፈጠራ እና የሰራተኞችን ክህሎት ማዳበር ላይ በጋራ መስራት ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር  ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚል ገለፁ፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ ይህን የገለፁት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር በጋራ መስራት በሚቻችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ለዜጎች ከፍተኛ የስራ እድል በመፍጠር ለሀገር እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አያይዘው ያነሱት ክብርት ሚኒስትሯ ይህንንም በይበልጥ ለማሳደግና ሰራተኞችን የበቁ ለማድረግ ፤ ክህሎታቸውን ይበልጥ ለማዳበርና እና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ከምንገዜውም በበለጠ ተቀራርቦ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡ 

እንደ ሚኒስትሯ ገለፃ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ ለዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ የሚፈጥራቸው የስራ እድሎች እንደ ሀገር ላለው የስራ እድል ፈጠራ እንቅስቃሴ አጋዥ በመሆኑ ይህንን አበረታች እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂም ጭምር በማስደገፍ እንቅስቃሴውን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ በጋራ መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከ2 ሚሊዮን በላይ የስራ እድሎችን የፈጠረ ሲሆን ከዚህ ውስጥም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቀጥተኛ የሆነ የስራ እድል በመፍጠር ትልቅ ድርሻ አለው።