• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 3 months, 3 weeks ago
  • 153 Views

የስራ እድል ፈጠራ እና ክህሎትን ማሳደግ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች የተፈጠረውን የስራ እድል ለማሳደግ ፤ ሰራተኞችን ብቁና ተወዳዳሪ ለማድረግና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ አያያዝ እንዲኖር እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ነፃ ንግድ ቀጠና የተፈጠረውን የስራ እድል በይበልጥ ለማሳደግ ፤ ሰራተኞችን ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ እና ከሰራተኞች ጋር የተገናኙ ዝርዝር መረጃዎችን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል። 

ይህ የተገለፀው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሀት ካሚል ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው። 

በውይይታቸውም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለዜጎች የሚፈጠር የስራ እድል እንዲያድግ ፤ ሰራተኞች ብቁ እና ልምድ ያላቸው እንዲሆኑ ብሎም ክህሎታቸውን በየጊዜው እንዲያሳድጉ በተጨማሪም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመደገፍ የሰው ሀይል ማስተዳደር ላይ በጋራ ሊሰራባቸው የሚችሉ ጉዳዮች በዝርዝር ተነስተዋል። 

በተጨማሪም ወደ ምርት ለመግባት ውል የፈረሙና የቅድመ ኦፕሬሽን ስራዎችን እያከናወኑ የሚገኙ አዳዲስ ባለሀብቶች ፤ ኢንቨስተሮችና አምራቾች በኢንቨስትመንት ለሚሰማሩባቸው ዘርፎች ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ሰራተኞችን በአጭር ግዜ እንዲያገኙ ለማስቻል በጋራ እንደሚሰራ ተመላክቷል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ኢትዮጵያ ውስጥ ለዜችጎ ከፍተኛ የስራ እድል ከሚፈጥሩ ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም ሲሆን በአሁን ሰዓት በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና ከ100 ሺ በላይ ቋሚ የስራ እድሎችን እንዲሁም ከ250 ሺ በላይ ቋሚ ያልሆነ የስራ እድል ለዜጎች ፈጥሯል።