ኮርፖሬሽኑ ከሁለት ሀገር በቀል የፋርማሲዩቲካል አምራቾች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሁለት ሀገር በቀል የፋርማሲዩቲካል አምራች ኩባንያዎች ጋር የውል ስምምነት በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ተፈራርሟል።
የውል ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የሁለቱ ኩባንያዎች ባለቤቶች ተፈራርመዋል ።
በፊርማ ስነ - ስርዓቱ ወቅት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እንደተናገሩት ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 1 ዓመታት ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት በፓርኮች ያሉ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ከነበረበት 10 በመቶ ወደ 55 በመቶ ማድረስ መቻሉን ገልፀው ፤በዚህኛው ንቅናቄም የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ መሆኑን ገልፀዋል ።
በዛሬው እለት የውል ስምምነት የተፈራረሙት ሁለት ኩባንያዎች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የለማ መሬት በመውሰድና የራሳቸውን ማምረቻ በመገንባት የሜዲካል ግሎቭ ፤ ዊልቼሮችን ፤ ስትሬቸሮችን እና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶችን የሚያመርቱ ይሆናል። ኩባንያዎቹ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ወጣት ዜጎችም የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
/