• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months ago
  • 196 Views

መሬታችንን ለባለሀብቶቻችን

"ኮርፖሬሽኑ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ከዚህ በፊት የነበረውን ቅድመ ክፍያ ከ10በመቶ ወደ 5 በመቶ ዝቅ አድርጓል" - አክሊሉ ታደሰ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ከዚህ በፊት የነበረውን ቅድመ ክፍያ ከነበረበት 10 በመቶ ወደ  5 በመቶ ዝቅ እንዲል ማድረጉን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ ገለጹ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ይህን የገለጹት በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩት ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነጻ የንግድ ቀጣና የሚገኙ የለሙ መሬቶችን በስፋት ለባለሃብቶች በተለይም አቅሙ ላላቸውና በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማሩ ሀገር በቀል ባለሀብቶች ለማስያዝ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡

ሃገራዊ የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ሪፎርሙን መሰረት በማድረግ እንደ ኮርፖሬሽን የተገበርናቸው የሪፎርም ስራዎች በኢንዱትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ተሳትፎ ማሳደግ መቻሉን አቶ አክሊሉ ጨምረው ገልጸዋል ።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በመድረኩ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ ብሎም በመጡበት ፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ በማሰብ ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የሊዝ ቅድመ-ክፍያ ከ10 በመቶ ወደ 5% በመቶ እንዲሁም የሼድ ኪራይን በፊት ከነበረበት የ 10 በመቶ ቅናሽ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

እንደ ኮርፖሬሽን የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ ሪፎርሞች ተግባራዊ መደረጋቸው ባለሀብቶቹ ወደ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት መነሳሳትን ፈጥሮላቸዋል ያሉት አቶ አክሊሉ በዚህም ካለፈው ሁለት ዓመት ወዲህ ከ60 በላይ ሀገር በቀል ባለሃብቶች የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው ወደ ስራ ገብተዋል ብለዋል፡፡ 

“መሬታችን ለባለሃብቶቻችን” በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት የተጀመረው የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ የለሙ መሬቶች ላይ ሰፊ የንቅናቄ ስራ በመስራት የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ለ2 ተከታታይ ወራትም የሚቆይ ይሆናል።

#Invest_in_Zero_Waiting_bureaucracy