• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 4 months, 1 week ago
  • 198 Views

ተጨማሪ የጃፓን ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች

"ተጨማሪ የጃፓን ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው" - በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር

ተጨማሪ የጃፓን ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና የነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጠንካራ ስራዎች እየተከወኑ መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ይህን የገለፁት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከአምባሳደሩ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ እና ጃፓን ካላቸው ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ጠንካራ ወዳጅነት አንፃር የጃፓን ኢንቨስተሮች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ያላቸው ተሳትፎና ድርሻ እንደሚጠበቀው አለመሆኑን ገልፀው ይህንን ለማሳደግ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህም ኮርፖሬሽኑ ከምንግዜውም በላቀ መልኩ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በኢንዱስትሪ ፓርኮች እያመረቱ የሚገኙ አለም ዓቀፍና ሀገር በቀል ኩባንያዎች አሁን ላይ ካላቸው ገበያ በተጨማሪ የጃፓንን ሰፊ የገበያ አቅም መጠቀም በሚችሉባቸው መንገዶች ላይ ምክክር ተደርጓል።

በቅርቡ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፓስፖርትን ጨምሮ ዓለም ዓቀፍ የደህንነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሚስጥራዊ የህትመት ውጤቶችን የሚያመርት ቶፓን ግራቪቲ የተሰኘ ግዙፍ የጃፓን ኩባንያ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወሳል።

'We are trying to attract more Japanese investors to invest in industrial parks' - Ambassador Shibata Hironori

Japan's Ambassador to Ethiopia Shibata Hironori stated that strong efforts are being made to encourage more Japanese investors to invest in industrial parks and Free Trade Zones in various investment sectors.

The ambassador disclosed this in a discussion held with IPDC CEO Aklilu Tadesse.

Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse, underlined to the ambassador that the share of Japanese investors in industrial parks is not as expected in related to the long-term relationship between Ethiopia and Japan and emphasized that strong cooperation is must to increase the investment flow. And he confirmed that IPDC is more ready than ever for this initiation.

In addition, discussions was made to enable international and domestic companies manufacturing in industrial parks to take advantage of Japan's huge market in addition to their current market.

Recently, a cornerstone stone was laid to build a giant Japanese company that produces secret printing products that meet international security standards, including passports, at Bole Lemi Industrial Park.

#Invest_in_Zero_Waiting_Time_bureaucracy