• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months ago
  • 541 Views

የኮሎምቢያው ኩባንያ የኢንቨስትመንት ፍላጎት

የኮሎምቢያ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በኢንቨስትመንት መሰማራት እንደሚፈልግ አሳወቀ 

ኮንሴፕቶስ የተሰኘ የኮሎምቢያ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በኢንቨስትመንት በመሰማራት ካገለገሉ የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶች ለኮንስትራክሽን የሚሆኑ ግብዓቶችን የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን ከፍተኛ አመራሮች በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። 

የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት ፍላጎታቸው ዝርዝር ማብራሪያ ለኮርፖሬሽኑ አመራሮች ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡ የቅድመ ኢንቨስትመንት ሀሳቦች ላይ ዝርዝር ውይፕት ተክልሂዷል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አክሊሉ ኩባንያው ያቀረበው የኢንቨስትመንት ሀሳብ ኮርፖሬሽኑ ከጀመረው 'Waste to Wealth' የተሰኘ ፕሮግራም ጋር ተያያዥ መሆኑና ለአገሪቱ ፅዱ ከባቢን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በእጅጉ የሚያግዝ በመሆኑ በአፋጣኝ ወደ ቅድመ ኢንቨስትመንት ተግባር መግባት እንዳለበት አሳስበዋል። 

ኩባንያው ያገለገሉ የፕላስቲክ ተረፈ ምርቶችን በመሰብሰብ እና በመጠቀም ለኮንስትራክሽን የሚውሉ ግብዓቶችን የሚያመርት ሲሆን በኮሎምቢያ ፤ በሌሎች የላቲን አሜሪካ ሀገራት እና በአይቮሪኮስት ተመሳሳይ ግዙፍ ኩባንያዎችን በማቋቋም በስራ ላይ ይገኛል። 

A Colombian company express its interest to invest in industrial parks 

Conceptos, a Colombian company, expressed its interest to invest in industrial parks to produce construction materials from used plastic waste. 

Industrial Parks Development Corporation CEO, received the senior management of the company in his office and spoke to them. 

The company's officials presented a detailed explanation of their investment needs to the corporation's management, and a detailed discussion was held on the pre-investment plans. 

IPDC CEO Mr. Aklilu, underlined that the investment proposal proposed by the company is related to the 'Waste to Wealth' program started by the corporation and will greatly help the effort to create a clean environment for the country, so that it should be put into pre-investment actions immediately. 

Conceptos is a colombian company produces materials for construction by collecting and using used plastic waste products, and it is operational and active in establishing similar giant companies in colombia , other Latin American countries and Ivory Coast.

#Invest_in_Zero_Waiting_Time_bureaucracy