የሳውዲ አረቢያ ኢንቨስተሮች በኢንዱስትሪ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የሳውዲ አረቢያ ኢንቨስተሮች በኢንዱትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው በማኑፋክቸሪንግ ፤ በፋርማሲዩቲካል እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የመሰማራት ፍላጎት ላላቸው የሳውዲ ኢንቨስተሮች ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህንን ጥሪ ያቀረቡት በዛሬው እለት በሳይንስ ሙዚየም በተካሄደው የኢትዮ-ሳውዲ የኢንቨስትመንትና ንግድ ፎረም ላይ ነው።
አቶ አክሊሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው 12 ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚገኙ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆኑ የመሰረተ ልማት አቅርቦቶችን ፤ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን እንዲሁም ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በተለያዩ ዘርፎች ለተሰማሩ የሳውዲ ባለሀብቶች አብራርተዋል።
በመጨረሻም ኮርፖሬሽኑ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎቱ ያላቸውን የሳውዲ ባለሀብቶች በቀልጣፋ አገልግሎትና ባጠረ ቢሮክራሲ ለማስተናገድ ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
Saudi Arabian investors were invited to invest in industrial parks
Aklilu Tadesse, Industrial Parks Development Corporation CEO, called on Saudi Arabian investors to invest in Industrial Parks and Dire Dawa Free Trade Zone.
Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadasse invited Saudi investors who are interested in investing in the Manufacturing, pharmaceutical and agro-processing and other sectors.
The CEO made this call at the Ethio-Saudi Investment and Trade held at the Science Museum today.
Ato Aklilu clarified for the saudi Investors engaged in various investment sectors about the Industrial Parks and Dire Dawa Free Trade Zone that IPDC built and manages and also he explained investment incentives, infrastructures and facilities as well as service efficiency.
Finally the CEO confirmed that the corporation is ready more than ever to accommodate Saudi investors who are interested in investing in industrial parks with efficient services and zero waiting bureaucracy.
#Invest_in_Zero_Waiting_Time_bureaucracy