ከ725 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት ያደረገው የቻይና ኩባንያ ምርት ማምረት ጀመረ
ከ725 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንቨስት ያደረገው አፍሉዌንስ የተሰኘው ኩባንያ የቅድመ ኦፕሬሽን ስራዎችን አጠናቆ በባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ምርት ማምረት ጀመረ፡፡
ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የውል ስምምነት ፈፅሞ በባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ የቅድመ ኦፕሬሽን ስራዎችን ሲያከናውን የቆየው አፍሉዌንስ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ በይፋ ምርት ማምረት መጀመሩ ተገልጿል።
ኩባንያው የተለያዩ ትራንስፎርመሮችንና ዲጂታል ቆጣሪዎችን በማምረት ለኢትዮጵያ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን በዚህም መንግስት በሃገራችን ያለውን የኤሌክትሪክ ሀይል ተደራሽነት ለማሳደግ ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡
ኩባንያው በ725 ሚሊዮን ብር ኢንቨስትመንት 5500 ካሬ ሜትር የማምረቻ ሼድ ተረክቦ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድልን እንደሚፈጥር የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ጥሩየ ቁሜ ገልጸዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላው ሃገሪቱ በተገነቡት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከኮርፖሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት የተፈራርሙ ባለሃብቶችን ወደ ስራ ለማስገባትና በአጭር ጊዜ ወደ ምርት ሂደት እንዲሸጋገሩ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ኮርፖሬሽኑ በአማራ ክልል ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ባህርዳር ፤ ኮምቦልቻ እና ደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ለኢንቨስትመንቶቹ መሳካትና ፍሰት መጨመር ሰላም ትልቁን ድርሻ ስለሚወስድ የአካባቢው ማህበረሰብና ወጣቱ ሰላሙን ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆን እንዳለበት መልክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡፡፡
The Chinese company, which invested more than 725 million birr, started production
Affluence, a company that has invested more than 725 million birr, has completed pre-operational work and started production at Bahir Dar Industrial Park.
The Chinese company Affluence, which has signed a contract agreement with Industrial Parks Development Corporation and has been doing pre-operational work at Bahir Dar Industrial Park, has officially started production.
The company is now producing various transformers and digital meters and supplying them to the Ethiopian market, and the investment will play a major role for government to increase access to electricity in our country.
General Manager of Bahr Dar Industry Park, Tiruye Kume, stated that the company has taken over a 5500 square meter production shed with an investment of 725 million birr, and when it starts production at full capacity, it will create job opportunities for more than 300 citizens.
Industrial Parks Development Corporation is providing the necessary support and supervision to the investors who have signed a contract with the corporation in the industrial parks built all over the country and to enable them to start the production process in a short period of time.
IPDC Deputy CEO, Zemen Junedi, noted that there are high investment demands in Bahir Dar, Kombolcha, and Debre Berhan Industrial Parks that the Corporation has built and manages in Amhara Region. He strongly emphasized that the local community and the youth should be committed to maintaining peace, as peace plays a major role in the success of the investments and the increase in their flow.