በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በክሪ የተመራ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ልዑክ ኢትዮጵያ ገባ
በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በክሪ የተመራ እና ከ80 በላይ አባላት ያለው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ልዑክ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ገብቷል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት የልዑክ ቡድኑን በ Golden Reception ፕሮግራም ተቀብለዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ለልዑኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በኢትዮጵያ በተለይም ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ግዙፍና አለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ማዕከላት የሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን ተመኝተዋል።
ልዑክ ቡድኑ በመጪዎቹ ቀናት ቆይታቸው ለቅድመ ኢንቨስትመንት ትግበራ እንዲረዳቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የሚያስተዳድራቸውን ቦሌ ለሚ ፤ ቂሊንጦ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።
የልዑክ ቡድኑ በፋርማሲዩቲካል ፤ በቴክስታይልና ጋርመንት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ያሉ አማራጮችን ይመለከታሉ።
Huge investment delegation headed by Jamal Bekri, the Ethiopian ambassador to Pakistan, entered Ethiopia.
A huge investment delegation led by Ethiopia's ambassador to Pakistan Jamal Bekri and consisting of more than 80 members arrived in Addis Ababa today.
Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse and the management members of the Corporation received the delegation with IPDC's Golden Reception programme.
The CEO of the corporation, Aklilu Tadesse, delivered a welcome message to the delegation and wished them success in their stay in Ethiopia, especially in the huge and world class investment centers managed by the corporation.
During their stay in the coming days, the delegation will visit Bole Lemi, Adama and Kilinto Industrial Parks which are managed by IPDC, to help them with pre-investment implementation.
The delegation will look at investment options in Pharmaceuticals, textiles and garments as well as other investment sectors.