• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 1 week ago
  • 638 Views

ኢትዮጵያ ታምርት 2016

"ኮርፖሬሽኑ ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱ አቅም ያላቸውን ሀገር በቀል አምራቾችና ባለሀብቶችን ማበረታታት ይቀጥላል" - አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አቅም ያላቸውን ሀገር በቀል አምራቾችና ባለሀብቶች ማበረታታት ይቀጥላል ሲሉ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ገለፁ።

አቶ አክሊሉ ይህን የገለፁት ከስራ አመራር አባላቶቻቸው ጋር በዛሬው እለት በሚሊኒየም አዳራሽ ተገኘተው የ2016 ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን በጎበኙበት ወቅት ነው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ከስራ አመራር አባላቶቻቸው ጋር በኤክስፖው የተሳተፉ ሀገር በቀልና የውጪ ኩባንያዎችን ምርቶችና እንቅስቃሴ ተዟዙረው ተመልክተዋል።

በምልከታቸውም የኩባንያ ባለቤቶችና አምራቾችን ያነጋገሩ ሲሆን ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና የሚገኙትን እንዲሁም በኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ የማምረት ፍላጎት ያላቸውን በተለይም ተኪ ምርቶችን የሚያመርቱና ለኢምፖርት የሚውጣ የውጪ ምንዛሪን ማስቀረት ላይ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ሀገር በቀል ኩባንያዎችና ባለሀብቶችን ማበረታታት እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy