"ተጨማሪ የጃፓን ኢንቨስትመንቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እየሰራን ነው" - ሺባታ ሄሮሪ
በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር የሆኑት ሺባታ ሄሮሪ ወደ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተጨማሪ እምቅ አቅም ያላቸው የጃፓን ኢንቨስትመንቶች እንዲመጡ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አምባሳደሩ ይህን የገለፁት በትናንትናው እለት ቶፓን ግራቪቲ የተሰኘ በዓመት 5.8 ሚሊዮን ፓስፖርቶች እንዲሁም 28 ሚሊዮን የሚሆኑ የተለያዩ የደህንነት ካርዶችን የማምረት አቅም ያለው የጃፓኑ ኩባንያ ማምረቻው በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲገነባ የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት ነው።
አምባሳደር ሺባታ እንደገለፁት ኤምባሲያቸው ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ሌሎች ኢንቨስትመንቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ተግባራዊ በሚደረግባቸው አግባቦች ላይ እየሰሩ መሆኑን አክለዋል።
አምባሳደሩ በስነ-ስርዓቱ ካደረጉት ንግግር በተጨማሪ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም ቶፓን ግራቪቲን የመሰሉ ሌሎች ግዙፍ የኢንቨስትመንት ካፒታልና አቅም እንዲሁም ልምድ ያላቸው ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በጋራ ለሚሰሩ ስራዎች አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
"We are striving to bring more Japanese investments to Ethiopia" - Shibata Hirori
Shibata Hirori, the Ambassador of Japan in Ethiopia, said that efforts are being made to bring more potential Japanese investments to Ethiopia's industrial parks.
The ambassador stated this yesterday when the corner stone was laid for the construction of a Japanese company called Topan Gravity, which has the capacity to produce 5.8 million passports and 28 million different types of security cards, at Bole Lemi Industrial Park.
Ambassador Shibata, pointed out that his embassy is working closely with Industrial Parks Development Corporation and added that they are working on ways to implement other Japanese investments in industrial parks.
In addition to his speech at the ceremony, the ambassador held a bilateral discussion with Aklilu Tadesse, Industrial Parks Development Corporation CEO.
In their discussion, they have together set a direction to work in cooperation to make other companies invest in industrial parks with huge investment capital and capacity and experience like Topan Gravity.
#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy