• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 2 weeks ago
  • 672 Views

የአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ የ8 ወራት አፈፃፀም

ባለፉት 8 ወራት በአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሃገር ውስጥ ገበያ ከቀረበ ምርት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች መካከል አንዱ የሆነው አረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ2016 በጀት ዓመት በ8 ወራት ውስጥ በፓርኩ የተመረቱ የተለያዩ ምርቶችን ለሃገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ማግኘት እንደተቻለ የኮርፖሬሽኑ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲን ገልፀዋል፡፡ 

ምክትል ስራ አስፈሚው እንደገለፁት በኢንዱስትሪ ፓርኩ የተለያዩ ተኪ ምርቶችን በማምረት ለውጭ ምንዛሬ ይወጣ የነበረን ከ19.4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማዳን የተቻለ ሲሆን በተለይም ሃገራችን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የምታወጣበትን የሴራሚክ ምርት በማምረት በኩል ትልቁን ድርሻ መወጣት መቻሉን አመላክተዋል፡፡ 

በአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካባቢ ከሚገኙ ነዋሪዎችና የሃገር ውስጥ አምራቾች ጋር ግብዓት ለማቅረብ  በተፈጠረ የገበያ ትስስር ባለፉት 8 ወራት ከ12.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር  በላይ  የገበያ ትስስር መፍጠር እንደተቻለ የተገለፀ ሲሆን የሴራሚክ ግብዓት እና የእንጨት ግብዓት ለፓርኩ የሚቀርቡ ዋነኛ ግብዓቶች መሆናቸውንም አቶ ዘመን ጨምረው ገልፀዋል። 

ባለፉት 8 ወራት ከ830 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አዳዲስ የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን አሁን ላይ ከ1500 በላይ የሚሆኑ ዜጎች በፓርኩ የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል። 

አሁን ላይ በአረርቲ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአጠቃላይ 3 ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በአልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ እንዲሁም በሴራሚክና እንጨት ስራ ላይ ተሰማርተው በምርት ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡ 

Arerti Industrial has been able to earn more than 1 billion birr from import substituted products in the last 8 months. 

Arerti Industrial Park, which is one of the investment centers managed by Industrial Parks Development Corporation, has been reported to have earned more than 1 billion birr by offering various products produced by the park to the domestic market in 8 months of the 2016 fiscal year said Zemen Junedin IPDC's Investment Promotion and Marketing division Deputy CEO. 

The Deputy CEO stated that more than 19.4 million US dollars were saved in the production of various import substituting products at the industrial park. 

Also Mr Zemen pointed out that more than 12.5 million US dollars market linkage have been created in the past 8 months through providing resources and raw materials to manufactures from the surrounding area. 

In addition to the market linkage and import substitution, in the last 8 months, more than 830 new jobs have been created for citizens, and now more than 1500 citizens have job opportunities in the park. 

Currently, there are 3 investors who have invested in Arerti Industrial Park and are engaged in the production process of garments and textiles as well as ceramics and wood products.

#invest_in_zero_waiting_time_bureaucracy