• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 3 weeks ago
  • 663 Views

የቻይናው CEEC ኩባንያ የአብረን እንስራ ጥያቄ

CEEC ኩባንያ በአዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እና በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መሰማራት እንደሚፈልግ ገለፀ 

የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ CEEC  በአዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እንዲሁም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር መስራት እንደሚፈልግ ገልጿል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን ዋና ስራ አኪያጅ ሸን ዠን እና ሌሎች ኃላፊዎችን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። 

የኩባንያው ኃላፊዎች አዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት፤ የግንባታ እና የኤሌክትሪካል ቁሳቁሶችን በማምረት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት ያለውን እቅድ በዝርዝር አቅርበዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ ከኩባንያው ጋር በጋራ ለመስራት ኮርፖሬሽኑ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመው ወደ ቀጣይ የቅድመ ኢንቨስትመንት ዝግጅት ምዕራፍ ለመሻገር ስራዎች እንዲጀመሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል። 

ተቀማጭነቱን ቻይና ያደረገው CEEC ከቻይና ውጪ በ140 ሀገራት ፕሮጀክቶች ያሉት ሲሆን፤ ከ130 ሺ በላይ ሰራተኞችን በማስተዳደር ከ60 ቢሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ትርፍ ያለው ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያ ነው። 

Chinese CEEC company showed interest to engage in the construction of new industrial parks and various investments 

The Chinese CEEC company stated that it would like to work in collaboration with Industrial Parks Development Corporation in the construction of new industrial parks as well as in various areas of investment. 

Industrial Parks Development Corporation CEO, received the General Manager of CEEC M.r Shen Zhen and other  officials of the company in his office and spoke to them. 

The company officials presented detailed plan to engage in manufacturing of cement and electrical materials as well as other investment sectors. 

The CEO, Aklilu Tadesse, pointed out that the corporation is ready to work together with the company and set the direction for the start of the process to move to the next phase of pre-investment preparation. 

CEEC, which made its base in China, is a huge international company with more than 130 thousand employees and more than 60 billion dollars of revenue with having projects in 140 countries outside of China.

#invest_in_zero_waiting_time_bureaucracy