• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 2 weeks ago
  • 732 Views

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ጉብኝት

"በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለወጣቶች በተለይም ለሴቶች የተፈጠረው የስራ እድል የሚበረታታ ነው" - ያኩብ ኤል ሂሎ 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ለወጣት ዜጎች በተለይም ለወጣት ሴቶች የተፈጠረው የስራ እድል አበረታች መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ትብብር የአፍሪካ ዳይሬክተር ያኩብ አል ሂሎ ገለፁ። 

ዳይሬክተሩ ይህን የገለፁት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እንዲሁም ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ፀሀፊና አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ ጋር የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴን በተመለከቱበት ወቅት ነው። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽናቸው እያከናወናቸው የሚገኙ ኢንቨስትመንት ተኮር ስራዎች ላይ እንዲሁም ፓርኩ ያለበትን ወቅታዊ የኦፕሬሽን እንቅስቃሴ አስመልክተው ሰፊ ገለፃ አድርገዋል። 

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ትብብር የአፍሪካ ዳይሬክተር ያኩብ አል ሂሎ በበኩላቸው በፓርኩ የተመለከቱት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንደሳባቸው በተለይም ለወጣት ሴቶች የተፈጠረው ሰፊ የስራ እድል አበረታች መሆንና ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል። 

"The employment opportunities created by IPDC for young people, especially women, are encouraging" - Yakub El Hillo 

Yacoub Al Hillo, Regional Director for United Nations Development Coordination office ( Regional office for Africa ) , said that the job opportunities created by industrial parks for young citizens, especially young women, are encouraging. 

The director stated this while he was visiting the current activities of Bole Lemi Industrial Park with Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse, and the Assistant Secretary and Coordinator of the United Nations, Dr. Ramiz Alakbarov. 

The CEO of the corporation, Aklilu Tadesse, made detailed explanation regarding the investment-related works being carried out by his corporation, as well as the current operational activities of Bole Lemi Industrial Park. 

On his part, Yacoub Al Hillo, Regional Director for United Nations Development Coordination office ( Regional office for Africa ), stated that he was attracted by the investment activities he saw in the park, especially the wide employment opportunities created for young women, which should be strengthened.