ኮርፖሬሽኑ ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝን ተግባራዊ አደረገ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓትን በዛሬው እለት በይፋ አስጀምሯል።
ፕሮግራሙን በይፋ ያስጀመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ናቸው።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ ፕሮግራሙን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት ኮርፖሬሽኑ በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ የጀመረው ሪፎርም ውጤታማነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል። አክለውም ለፕሮግራሙ አተገባበርና ስኬታማነት ሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም የመሬትና መሰረተ ልማት ዘርፍ አመራሮችና ሰራተኞች ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ኮርፖሬሽኑ በዛሬው እለት ተግባራዊ ያደረገው ዘመናዊ የመሬት መረጃ አያያዝ ስርዓት በኮርፖሬሽኑ የሚተዳደሩ መሬቶችን በጠቅላላ መረጃቸውን ዲጂታላይዝ በሆነ መንገድ ለመያዝ፤ የሊዝ እና የኪራይ መረጃዎችን በዘመናዊ ሲስተም በአግባቡ መዝግቦ ለመያዝና ለመከታተል እንዲሁም ሪፖርት ለመቀበል እና አጠቃላይ ከመሬት ጋር ተያይዞ ያለውን አጠቃለይ እንቅስቃሴ በሲስተም ማከናወን የሚያስችል ነው።
በፕሮግራሙ ላይ የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኃላፊዎች እንዲሁም በፕሮጀክቱ ተሳታፊ የነበሩ አካላት ተሳትፈዋል።