• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 1 week ago
  • 514 Views

300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያስመዘገበው የቻይና ኩባንያ

300 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይና ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ 

300 ሚሊዮን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ የተሰኘ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኩባንያውን አመራሮች በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። 

የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት እቅዳቸው ዝርዝር መረጃዎችን ያቀረቡ ሲሆን የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን፤ ማበረታቻዎችን እንዲሁም የመሰረተ ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን የተመለከቱ መረጃዎችን አቅርበዋል። ኢንቨስትመንቱ እንዲሳካና እውን እንዲሆንም ኮርፖሬሽኑ ያልተቋረጠ ድጋፍ እንደሚያደረግ አረጋግጠዋል። 

ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ እ.አ.አ በ2011 የተቋቋመና ተቀማጭነቱን በቻይና ያደረገ ኩባንያ ሲሆን በሳውዲ አረቢያ፤ በጋና፤ በናይጄሪያ፤ በኢራን እንዲሁም በአዘርባጃን የፋይበር፤ በሴራሚክ፤ በአልሙኒየም እና በሌሎች የምርት አይነቶች ተሰማርቶ የሚገኝ ግዙፍ ኩባንያ ነው። 

በተጨማሪም የኩባንያው የስራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ የሚገኘውን ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የጎበኙ ሲሆን በፓርኩ ለባለሀብቶች የሚቀርቡ እንደ መብራት፤ ውሀ እና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶች ክፍያ ከሌሎች ተመሳሳይ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑን እና ይህም ለኢንቨስትመንት ውሳኔያቸው ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ገልፀዋል። 

Chinese company with a capital of 300 million USD is interested in manufacturing in industrial parks 

Wenzhou Nixin Trading, a company with an investment capital of $300 million, has expressed its interest in producing paper in industrial parks. 

Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse, received the officials of the company in his office and discussed with them. 

The officials of the company presented detailed information about their investment plans, and IPDC CEO, Aklilu Tadesse, briefed them about the investment centers in the corporation, incentives as well as infrastructure and service delivery. 

Wenzhou Nixin Trading is a company that was established in 2011 and located in China. The company has 6 production bases around the world in Saudi Arabia, Ghana, Nigeria, Iran and Azerbaijan and is producing Fiber, Ceramics, Aluminum and other types of products. 

In addition, the company's officials visited Bole Lemi Industrial Park in Addis Ababa, where the park offered to investors such as electricity, water and telecommunications services with better price compared to other similar countries and they stated this will play a big role in their investment decision.