• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 2 weeks ago
  • 466 Views

ሀገራዊ የ2016 የመጀመሪያ 6 ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ አመላካች አፈፃፀሞች

"በሀገር አቀፍ ደረጃ ለተመዘገበው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እድገት የኮርፖሬሽኑ ሚና ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል" - አክሊሉ ታደሰ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያቤትና የቅርንጫፍ ፓርኮች አመራርና ሰራተኞች የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የመንግስት ስራዎች እቅድ አፈፃፀምን ገምግመዋል። 

የግምገማ መድረኩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ባለፉት 6 ወራት በሁሉም ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ የንግድ ቀጠና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትና በዘርፉ ውጤት ለማስመዝገብ የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች የሀገርን ማክሮ ኢኮኖሚ በማሳደግና የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል ትልቅ  ሚና እንደነበረው ገልፀዋል። 

በማኑፋክቸሪንጉ ዘርፍ ለተመዘገቡት አገር አቀፍ ውጤቶች በኮርፖሬሽኑ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ  የተሰራው ሪፎርም  በተለይም ምቹ የስራ ከባቢ በመፍጠር ፤ አገልግሎቱን  ዲጂታላይዝድ በማድረግ ፤ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ያለምንም መጉላላት ተደራሽ በማድረግ እና ከተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር በኩል የተሰሩት ስራዎች ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸውና በቀጣይም ለማክሮ ኢኮኖሚው እድገት የራሱን አሻራ ለማሳረፍ  የተጀመረውን ሪፎርም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አቶ አክሊሉ ጨምረው ገልጸዋል፡፡ 

በሌላ በኩል ተኪ ምርቶችን በማምረትና የውጪ ምንዛሪን በማዳን በኩል ብሎም ለወጣት በተለይም ለሴት ዜጎች የተፈጠሩ እድሎች ከፍተኛ ውጤት የታየባቸው መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው አስታውሰዋል። 

በግምገማ መድረኩ የኮርፖሬሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ፤ የቦሌ ለሚና ቂሊንጦ ኢንዱሰትሪ ፓርኮች ፤ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት እንዲሁም የአዲስ ኢንዱስትሪ መንደር  አመራርና ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ለመድረኩ የተለያዩ ገንቢ ሀሳቦችን አካፍለዋል።