• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 7 months, 3 weeks ago
  • 461 Views

የኮርፖሬሽኑና የጂ አይ ዜድ ( GIZ ) ጥምረት

"በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የዜጎች ብዝሃ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል" - አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ በጂአይዜድ ስር እየተተገበረ ያለው የዘላቂ ኢንደስትሪ ክላስተር ፕሮጀክት (Sustainable Industrial Cluster Project) ኃላፊ የሆኑትን አና ዋልድማንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው ከኃላፊዋ ጋር በነበራቸው ውይይት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፤ የስራ እድል ፈጠራን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና የፓርኮችን ልማት ለማጠናከር በዘርፉ ዙሪያ የሚሰሩ አጋር ድርጅቶች ሚና ጉልህ መሆኑን አስታውሰው በቀጣይም ከጂአይዜድ ኢትዮጵያ ጋር በትብብር በመስራት ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

በጂ አይ ዜድ ስር እየተተገበረ የሚገኘው የዘላቂ ኢንደስትሪ ክላስተር ፕሮጀክት ኃላፊ አና ዋልድማን በበኩላቸው ከኮርፖሬሽኑ ጋር በመተባበር በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በርካታ ስራዎች  ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ገልጸው በቀጣይም ትብብራቸውን በማጠናከር ለተሻለ ውጤት እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ኃላፊዎቹ በነበራቸው ውይይት  እስካሁን በጋራ የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ በጋራ በሚሰሩባቸው በሰው ሀይል ልማት ፤ በስልጠና ፤  በፓርኮች ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን ትብብራቸውን አጠናክረው ለማስቀጠል የሚያስችል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

'Cooperation with partner organizations should be strengthened in order to ensure the multi-use of citizens in industrial parks' - Aklilu Tadesse

Aklilu Tadesse, IPDC CEO, received and discussed with Anna Waldman, Sustainable Industrial Cluster Project head under GIZ , at his office.

The CEO reminded that the role of partner organizations working in the sector is significant in order to strengthen the creation of job opportunities, to strengthen the development of parks and to ensure the universal benefit of workers working in industrial parks. He added that the partnership with GIZ Ethiopia should be positively strengthen.

Anna Waldman, Sustainable Industrial Cluster Project head under GIZ, said that they have been working with IPDC in various industrial parks and will continue to work for effective results by strengthening their cooperation.

In the discussions held by the officials today, the works done together so far were evaluated, and they discussed the human resource development, training and  development of parks and related issue where they will work together in the future and reached a consensus to strengthen their cooperation.