የህክምና ቁሳቁስ አምራቾች በኢትዮጵያ ለምን ኢንቨስት ያደርጋሉ?
በኢትዮጵያ ያለው የፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ከውጪ በሚመጡ ( Import ) በሚደረጉ ምርቶች ላይ ጥገኛ ነው፤ ሀገር ውስጥ የሚገኙ በጣት የሚቆጠሩ የሀገር ውስጥ አምራቾች 10 በመቶ የሆነውን ምርት በማምረት ግማሽ ቢሊዮን ዶላር ለሚገመተው ግዙፍ የዘርፉ ገበያ ውስን የህክምና መድሐኒቶችን፤ የህክምና መሳሪያዎችን እና የህክምና ግብዓቶችን ያቀርባሉ።
ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት የሀገር ውስጥ ምርቶችን/ተኪ ምርቶችን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታን በማበጀትና ለፋርማሲዩቲካል ልማት ዘርፍ ቅድሚያ በመስጠት እና ቁርጠኛ የመንግስት አካላትን በማቋቋም ውጤታማ የፖሊሲ ትግበራ በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል።
የሀገሪቱ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት፤ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻሎች ፤ የማህበራዊ ጤና መድህን ሽፋን በመላ ሀገሪቱ መስፋፋት፤ የህብረተሰቡ የጤና ግንዛቤ ማደግ ፤ የምርምር እና የህክምና ዘርፍ መስፋፋት በኢትዮጵያ እየጨመረ ላለው የፋርማሲዩቲካል ምርቶች ፍጆታ ዋነኛ ማሳያዎች ናቸው።
ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሀገር ውስጥም በውጪም ግዙፍ ገበያ ባለውና በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ በሚገኘው ለዚሁ ዓላማ በተገነባው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ሀገር በቀልና የውጭ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ይጋብዛል።
ኮርፖሬሽኑ በፋርማሲዩቲካል እና በሌሎች ተያያዥ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች መሰማራት ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የለማ መሬት ከተሟላ መሰረተ ልማት ጋር አቅርቦ አምራቾችን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ይምጡ!
በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ፤ በፋርማሲዩቲካ ዘርፍ ኢንቨስት ያድርጉ!
Why should pharmaceutical manufacturers invest in Ethiopia?
The pharmaceutical sector in Ethiopia is heavily import-dependent, hosting few domestic producers supplying less than 10% to a half a billion-dollar market, producing limited therapeutic drugs, medical supplies/instruments and medical apparatus, and veterinary medicines.
The Government of Ethiopia prioritized the development of the pharmaceutical sector by tailoring enabling environment to enhance domestic manufacturing and established dedicate government organs for effective policy implementation.
The country’s strong economic growth, improvements in the delivery of health care services, the introduction of social health insurance coverage across the country, and increasing public health awareness and disposable income, diagnosis, and treatment are indicators for a surge in pharmaceutical products consumption in Ethiopia.
Industrial Parks Development Corporation (IPDC) invites investors (domestic and foreign) to invest in Kilinto Industry Park which is found in Addis Ababa close to Bole International Airport.
Serviced land for pharmaceutical and other manufacturing sectors is available for sub lease to the potential investors in this industry park.
Come and Invest in Kilinto Industrial Park፡ The pharmaceutical manufacturing Hub!
#Invest_In_Zero_Waiting_Time_bureaucracy