"ሴቶችን እናብቃ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!"
አለም ዓቀፉ የሴቶች ቀን ( March 8 ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤትና በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተከብሮ ውሏል።
እለቱ በዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሚገኙ አመራርና ሰራተኞች በተለያዩ መርሀ ግብሮች ተከብሯል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በመላው ሀገሪቱ ገንብቶ በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረላቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
ኮርፖሬሽኑ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንደ ወትሮው ሁሉ ለማረጋገጥ እንደሚሰራ በበዓሉ አከባበበር ላይ ተገልጿል።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ( March 8 ) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ48ኛ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
#March8