የዱባዩ አርማዳ ሆልዲንግ ግሩፕ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የተሰማራውና ከ20 በላይ ኩባንያዎች በስሩ የሚገኙት አርማዳ ሆልዲንግ ግሩፕ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ የንግድ ቀጠና ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከስራ አመራር አባላቶቻቸው ጋር ከግሩፑ ባለቤት ዶ/ር መሀመድ ራሂፍ ሀኪሚ ጋር በበይነ መረብ ውይይት አድርዋል።
የሆልዲንግ ግሩፑ ባለቤት ዶ/ር ሀኪሚ ኩባንያዎቻቸው የተሰማሩባቸውን የፋርማሲዩቲካል ፤ የግብርና ምርቶች ማቀነባበር እንዲሁም የሪልስቴት እና የአገልግሎት ኢንቨስትመንት ሴክተሮች በኢትዮጵያ በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና የማስፋፋትና ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ለኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽናቸው እንደወትሮው ለቀጥታ የውጪ ኢንቨስትመንት የሚሰጠውን ትኩረትና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርም አስታውሰው ግሩፑ በሚሰማራበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊ ድጋፎች የሚደረጉለት መሆኑን አረጋግጠዋል።
ተቀማጭነቱን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያደረገው አርማዳ ሆልዲንግስ ግሩፕ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከ20 የሚበልጡ ኩባንያዎች በስሩ የሚተዳደሩ ሲሆን በፋርማሲዩቲካል ፤ በሪልስቴት ግንባታ፤ በኮንትራትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት እንዲሁም በቅንጡ ሆቴሎች ግንባታ የተሰማራ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ግሩፕ ነው።
The Dubai Group, which owns more than 20 companies, expressed its interest to invest in Industrial parks.
Armada Holding Group, which is engaged in various investment sectors in United Arab Emirates and owns more than 20 companies, expressed its desire to invest in industrial parks and free trade zones.
Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse, along with his management members, held an online discussion with the group's owner, Dr. Mohammad Rahif Hakimi.
The owner of the holding group, Dr. Hakimi, stated that he is interested in expanding the group's investments in and to invest in industrial parks and free trade zones in pharmaceuticals, Agro processing, real estate and service investment sectors in Ethiopia.
IPDC CEO, Aklilu Tadesse, said that the attention and efficient service delivery of his corporation as usual is ready for foreign direct investment and confirmed that the necessary support will be given to the group in order to make the investment successful.
Armada Holdings/Armada Group is one of the leading United Arab Emirates conglomerates with more than 20 active companies having diversified interests in different countries spanning across healthcare, hospitality, real estate investment property development, as well as construction.
#Invest_In_Zero_Waiting_Time_bureaucracy