• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 1 week ago
  • 477 Views

ተጨማሪ ኢንቨስትመንትና የስራ እድል በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ

ሺንትስ ኩባንያ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ፈሰስ በማድረግ የሰራተኞቹን ቁጥር 20 ሺ ለማድረስ ማቀዱን ገለፀ 

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው ሺንትስ የተሰኘው የደቡብ ኮሪያ የጋርመንትና ቴክስታይል ኩባንያ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ፈሰስ ለማድረግና ከ15ሺ በላይ ለሚሆኑ  ዜጎች ተጨማሪ የስራ እድል በመፍጠር የሰራተኞቹን ቁጥር 20 ሺ ለማድረስ ማሰቡን ለኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አሳውቋል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ከገቡት የኩባንያው ፕሬዚዳንትና ባለቤት ቻ ሚን ሆን ጋር ተወያይተዋል። 

በውይይታቸውም የሺንትስ ኩባንያ ባለቤት ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ካፒታል ፈሰስ በማድረግ አሁን ካሏቸው 6ሺ ሰራተኞች በተጨማሪ ለ15 ሺ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኩባንያው እያደረገ ላለው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ አመስግነው ለተጨማሪ ኢንቨስትመንት አስፈላጊ የሆኑትን የመሬትና የመሰረተ ልማት አቅርቦቶች መሟላት ኮርፖሬሽኑ እንደሁልጊዜውም አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል። 

ሺንትስ የጨርቃጨርቅና ጋርመንት ኩባንያ መሰረቱን ደቡብ ኮርያ ያደረገ ሲሆን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ማምረቻ ሼዶችን በመውሰድና ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል ፈሰስ በማደረግ ስራ የጀመረና ከ6 ሺ በላይ ሰራተኞችን ቀጥሮ እያሰራ ያለ አለም አቀፍ የጨርቃ ጨርቅና ጋርመንት አምራች ኩባንያ ነው። 

የኩባንያው ባለቤትና ፕሬዚዳንት በዛሬው እለት አዲስ አበባ ሲገቡ በኮርፖሬሽኑ እየተተገበረ ባለዉ የ Golden Reception VIP ፕሮግራም አቀባበል ተደርጎላቸዋል። 

ጎልደን ሪሴፕሽን ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከላት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡ ፤ የስራ እድል ፈጠራቸው ከፍተኛ የሆነና ለማክሮ ኢኮኖሚክ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው ኢንቨስተሮች ወደ ሀገር ሲገቡ ልዩ ሳሎን መግቢያ (VIP) እንዲመቻችላቸው ፤ ከአየር መንገድ እስከ ሆቴልና ማረፊያቸው ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት በተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊ አሸከርካሪነት እንዲሰጣቸው እና የተቋሙ የበላይ ሀላፊዎችም የክብር እጅባ እንዲያደርጉላቸው የሚያደርግ አዲስ አሰራር ሲሆን በቆይታቸው ሁሉ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ፣  የሆቴል መስተንግዶ እንዲያገኙና የሀገራችንን ባህላዊ የቡና ስነ-ስርዓት እንዲጋበዙ የሚያስችል አገልግሎት ነው። 

Shints Company shows interest for additional investment 

Shints, a South Korean garment and textile company located in Bole Lemi Industrial Park, has informed IPDC that it intends to invest more and create more jobs for more than 15,000 citizens. 

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, had a discussion with the president and owner of the company, CHA MIN HO, who arrived in Addis Ababa today. 

In their discussion, the owner of Shints Company stated that they are ready to create job opportunities for 15 thousand citizens in addition to the 6 thousand employees they currently have by adding more investment. 

IPDC CEO, Aklilu Tadesse, thanked the company for the high level of investment that the company is successfully  operating  and confirmed that the corporation will respond as always to the completion of the necessary land and infrastructure supplies for further investment. 

Shints Textile and Garment Company is an international textile and garment manufacturing company based in South Korea. The company has started its operation in 2014 by taking production sheds in Bole Limi Industrial Park and investing a large amount of investment capital and employing more than 6,000 employees. 

When the company's owner and president arrived in Addis Ababa today, they were welcomed by the Golden Reception VIP program implemented by IPDC. 

Golden Reception is a VIP service for anchor  investors with high investment capital and whose job creation is high also who contribute significantly to macroeconomic growth. By the service they will be given a service of special entrance (VIP), transportation from the airline to their hotel by the head of IPDC, hand of honor by top officials of institutions including IPDC, and they will get transportation services throughout their stay, receive hotel hospitality upon arrival, and enjoy the traditional coffee ceremony of our country.

#Golden_Reception