• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 1 week ago
  • 203 Views

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎትና ሰመራ ዩኒቨርሲቲ

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ 

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በዛሬው እለት የሁለትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርመዋል። 

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን እና የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን ናቸው። 

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት እንዳስቀመጡት አገልግሎቱ ላለፉት 40 ዓመታት ያካበተውን ልምድ በመጠቀም ዩኒቨርሲቲው ያነገበውን ግብ እንዲያሳካ ጥረት እንደሚደረግ አረጋግጠው ከተቋማት ጋር የሚደረጉ መሰል ግንኙነቶችና ስምምነቶች ለሀገራዊ እድገት ያላቸው አስተዋፅኦ ቀላል እንዳልሆነ ገልፀዋል። 

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን በበኩላቸው ስምምነቱ ሰመራ ዩኒቨርሲቲን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች በእጅጉ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰው ለውጤታማነቱ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አስታውሰዋል። 

ሁለቱ ተቋማት በዛሬው እለት የተፈራረሙት መግባቢካ በሁሉም የሁለትዮሽ ዘርፍ የጠነከረ ግንኙነትና ትብብር እንዲኖር፤ የተለያዩ የጥናት ፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን በጋራ ለማዘጋጀትና ለመጠቀም ፤ በሰው ሀብትና በተለያዩ አገልግሎቶች ተቀራርቦ ለመስራት፤ የስልጠናና ማማከርና አገልግሎቶችን ለመስጠት እና በሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ መሆኑ ታውቋል። 

ከስምምነቱ ባሻገር በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሙዚየም ጉብኝት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የጋራ ስራዎች ላይም ዝርዝር ውይይት ተደርጓል። 

Industrial Projects Service ( IPS ) signed a memorandum of understanding with Samara University  

A memorandum of understanding was signed by Industrial Parks Development Corporation's Industrial Projects Service ( IPS ) with Samara University. 

The MoU was signed by General Manager of Industrial Projects Service Mr. Shiferaw Solomon and President of Samera University Dr. Mohammed Usman. 

During the MoU signing ceremony, the General Manager of Industrial Projects Service ( IPS ) confirmed that the service will make efforts to achieve the university's goals by using the experience it has accumulated over the past 40 years. He also stated that the contribution of such relations and agreements with institutions to national development is huge. 

The President of Samera University, Dr. Muhammad Usman, said that the agreement will greatly help the work being done to make Samera University a center of excellence and reminded that it is important to work together for its effectiveness. 

The two institutions signed the memorandum of understanding today to ensure strong relations and cooperation, to jointly prepare and use various research project proposals, to work closely with human resources and facilities with various services and so on. The MoU also aims to provide training, consulting and services to work together on in collaboration. 

Apart from the agreement, a visit was made to Samara University Museum and detailed discussions were held on future collaborations.

#IPS