የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለአፋር ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽር ያዘጋጃቸውን ጥናቶች አስረከበ
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለአፋር ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሰራቸውን ጥናቶች በይፋ አስረክቧል።
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጥናቶቹን ለአፋር ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ወ/ሮ አይሻ መሀመድ በይፋ አስረክበዋል።
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ጥናቶቹ ብዙ የተደከመባቸውና በትልቅ ትኩረትና ጥራት የተሰሩ መሆናቸውን አስታውሰው ጥናቶቹ ተግባራዊ በአጠረ ግዜ እንዲሆኑ በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ለክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያጠናው ጥናት በክልሉ ከሚገኙ 41 ወረዳዎች የ19ኙን ወረዳዎች የኢንቨስትመንት እምቅ ሀብት መለየት እና የኢንቨስትመንት ሀሳቦችን ፕሮፋይል ማዘጋጀት
ሲሆን በጥናቱ 110 የኢንቨስትመንት ሀሳቦች የታዩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ 32 ፕሮጀክቶች ተለይተው ቀርበዋል።
ጥናቱ አፋር ክልል ያለውን የኢንቨስትመንት እና የተፈጥሮ ሀብት እምቅ ሀብት ተቀሞ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ እና አዳዲስ የቢዝነስ ሀሳቦችን ተግባራዊ ለማድረግ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተጠቁሟል።
በቀጣይም በቀሪ ወረዳዎች ላይ የተለያዩ ጥናቶችን ለመስራት ከስምምነት የተደረሰ ሲሆን በጋራ መስራት በሚቻልባቸው በሌሎች መስኮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
Industrial Projects Service ( IPS ) officially submitted studies for Afar Region Investment Commission
IPDC's Industrial Projects Service ( IPS ) officially submitted the studies done for the Afar Region Investment Commission.
Industrial Projects Service General Manager
Mr. Shiferaw Solomon officially handed over the studies to Mrs. Aisha Mohammed, Commissioner of Afar Region Investment Commission.
Speaking during the handover ceremony, Mr. Shiferaw Solomon, General Manager of Industrial Projects Service, reminded that the studies were done with great attention and quality and emphasized the importance of working collaboratively so that the studies can be implemented in a short period of time.
The study conducted by Industrial Projects Service ( IPS ) for the Regional Investment Commission identified the investment potential of 19 woredas out of 41 in the region and prepared a profile of investment proposals. In the study, 110 investment ideas were seen, of which 32 investment projects that should be prioritized were identified.
The study will be important to attract investments and implement new business ideas usinh natural resource potential the Afar region.
Further, an agreement was reached to conduct various studies on the remaining woredas, and a discussion was held on other areas where it is possible to work in collaboration.
#IPS