• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months, 1 week ago
  • 514 Views

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና አስተባባሪ መልዕክት

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የስራ እንቅስቃሴ አበረታች ነው - ዶ/ር ራሚዝ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ እና አስተባባሪ ዶ/ር ራሚዝ አላክባሮቭ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለው የስራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገለፁ።

ረዳት ዋና ፀሐፊው ይህን የገለፁት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር በመሆን የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው በተመለከቱበት ወቅት ነው።

ዶ/ር ራሚዝ ከዋና ስራ አስፈፃሚው ጋር በመሆን አጠቃላይ የፓርኩን እንቅስቃሴ የተመለከቱ ሲሆን በፓርኩ የሚገኙ ሱፍሌ እና ጄጄ ኩባንያዎችን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት ተመልክተዋል። የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የፓርኩንና የኮርፖሬሽኑን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዎች በተለይም ከስራ ዕድል ፈጠራ ፤ ከአካባቢ ጥበቃ ፤ ከገበያ ትሰስርና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ጋር የተያያዘ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር ራሚዝ በፓርኩ የተመለከቱት የስራ እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልፀው በተለይም ኮርፖሬሽኑ ለሀገር በቀል ኩባንያዎችና ባለሀብቶች የሰጠው ልዩ ትኩረት እንዲሁም የአርሶአደሮች የገበያ ትስስር ፤ የወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ፈጠራ እና ኤክስፖርት ላይ እየተከናወኑ ያሉት አበረታች ስራዎች ሀገሪቱ የያዘችውን የኢንዱስትሪያላይዜሽን ግብና የምዕተ አመቱን እና የዘላቂ ልማት ግብ በአጭር ጊዜ ለማሳካት ትልቅ አቅም መሆኑን ከኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ጋር በተወያዩበት ወቅት አንስተዋል።

ከምልከታው ባሻገርም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋር በቅርርብ መስራት በሚችልባቸው የተለያዩ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ኃላፊዎቹ ውይይት ተደርጓል።

The promising activities in industrial parks are encouraging - Dr. Ramiz

Dr Ramiz Alakbarov, UN Assistant Secretary General, UN Resident and Humanitarian Coordinator stated that the promising activities in industrial parks are encouraging.

The Assistant Secretary General stated this when he toured Bole Limi Industrial Park together with Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse.

Dr. Ramiz along with IPDC CEO observed the overall activity of the park and observed the activities of two companies named Souffle and JJ located in the park. IPDC CEO, Aklilu Tadesse, gave an explanation about the park and the general activities of the corporation.

The United Nations Assistant Secretary General, Dr. Ramiz, said that the promising activities they saw at the park was encouraging, especially the attention given by IPDC to local companies and investors, as well as market linkages. He additionally pointed out that works being done on job creation and export is a great potential to achieve the industrialization goal of the country.

Apart from the visit, the officials discussed the possible conditions under which Industrial Parks Development Corporation can work in coordination with the United Nations.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_bureaucracy