• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 5 months, 2 weeks ago
  • 208 Views

157 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶች

ባለፉት 6 ወራት 157 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉ ተገለፀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ባለፉት 6 ወራት 157 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉ ተገልጿል።

በድሬዳዋ በተካሄደው የኮርፖሬሽኑ የግምገማ መድረክ ምርቶቹን በሀገር ውስጥ በማምረት እና በመተካት ምርቶቹን ወደ ሀገር ለማስገባት ይወጣ የነበረውን ዶላር ማስቀረት መቻሉ ትልቅ እምርታ መሆኑ ተመላክቷል።

ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ92 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን በማምረት ቀዳሚውን ድርሻ ሲይዝ አዳማ፤ አረርቲ፤ ደብረ ብርሀን እና ሌሎች ኢንዱስትሪ ፓርኮች በየደረጃው ይከተላሉ።

በዘርፉ የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈፃፀም ካለፈው ሁለት አመታት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ብልጫ ያለው መሆኑም ተነስቷል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከተቋቋመበት ግዜ አንስቶ ከ573 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ተኪ ምርቶችን በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ ችሏል።

IPDC Produced products worth 157 USD to substitute import

It has been stated that Industrial Parks development Corporation have been able to produce products worth approximately 157 million dollars in the last 6 months to substitute import from its industry parks and Dire Dawa Free Trade Zone.

It was pointed out in the corporation's performance evaluation event held in Dire Dawa that IPDC was able to replace the dollars that would be spent to import products by producing products in the investment centers.

Bole Lemi Industrial Park took the lead in producing the products worth more than 92 million dollars. Adama, Arerti, Debre Birhan and other industrial parks will follow accordingly.

It was also pointed out that the performance of 6 months of the 2016 fiscal year in the sector is significantly higher compared to the previous two years.

Since its establishment, Industrial Parks Development Corporation has been able to supply the domestic market with products worth more than 573 million dollars.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy