የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የታሰበለትን ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸው ተገለፀ
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አመራሮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አመራሮች ጋር በመሆን የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
አመራሮቹ በነፃ ንግድ ቀጠናው የሚገኙ የፓኬጂንግ እና የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ኩባንያዎችን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው የተመለከቱ ሲሆን ነፃ ንግድ ቀጠናው የታሰበለትን ሀገራዊ ዓላማ ለማሳካት እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልፀዋል።
አመራሮቹ በነፃ ንግድ ቀጠናው ከነበራቸው ጉብኝት ጎን ለጎን አምራች ኩባንያዎቹ በዘርፉ እየገጠሟቸው የሚገኙ የተለያዩ ተግዳሮቶች ላይ ከኩባንያ ባለቤቶችና ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል።
#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy