• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months, 2 weeks ago
  • 484 Views

የአስተዳደሩ ግምገማ

በግማሽ ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠልና በቀጣይ መሻሻል ለሚገባቸው ጉዳዮች ትኩረት መስጠት ይገባል ተባለ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በ2016 በጀት ዓመት ባለፉት 6 ወራት የነበረውን የእቅድ አፈፃፀም ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር አመራሮች በዛሬው እለት በድሬዳዋ አቅርቧል። 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የስራ አመራር አባላት ዋና ዋና በሚባሉ አመላካች የትኩረት አቅጣጫዎችና እቅዶች ላይ የነበረውን የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይም ዝርዝር ውይይት ተደርጓል። 

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሀይለሚካኤል ኮርፖሬሽኑ በግማሽ ዓመቱ ያስመዘገባቸው ዘርፈ ብዙ አበረታች ውጤቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፤ የሪፎርም ተግባራት ክንውን እያደገ እንዲመጣ እንዲሁም መሻሻል የሚገባቸውና በቀጣይ የበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዜያት ትኩረት የሚሹ አፈፃፀሞች ላይ የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንዲቻል በርብርብ መስራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል። አቶ ሀብታሙ አክለውም  ኮርፖሬሽኑ በማኑፋክቸሪንግ ፤ በኢንዱስትሪ ቴክኖሎጂ ሽግግር ፤ በተኪ ምርትና በኢንዱስትሪ ሊንኬጅ ላይ ባለፉት 6 ወራት ያስመዘገበዉ ዉጤት አበረታችና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን አንስተዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው አስተዳደሩ ከእቅድ ዝግጅትና ትግበራ ጀምሮ የመስክ ጉብኝቶችንም ጭምር በማድረግ ለኮርፖሬሽኑ ውጤታማነት ለሚያደርገው ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።