• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months, 3 weeks ago
  • 548 Views

ሚትስቡሺ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና

ሚትስቡሺ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በትሬዲንግ ኢንቨስትመንት የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

እውቁና አለም ዓቀፉ የመኪና አምራች ሚትስቡሺ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በትሬዲንግ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመጠቀም ፍላጎት እንዳለው ለኮርፖሬሽኑ ገልጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲን የኩባንያውን ስራ አስኪያጅ ሺግዮሺን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የኩባንያው ስራ አስኪያጅ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች መካከል ሐዋሳ፤ አዳማ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መጎብኘታቸውንና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናም ከትሬዲንግ ጋር የተያያዙ ኢንቨስትመንቶች ላይ መሰማራት እንደሚፈልግ ገልፀዋል። አያይዘውም ኩባንያው ለኢንቨስትመንቱ የሚረዱ ቅድመ ጥናቶችን ማከናወን እንደሚፈልግ አስረድተዋል።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን በበኩላቸው ድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና አሁን ላይ በኢንቨስትመንት ትልቅ ፍላጎትና የተለያዩ ዘርፎችን እያስተናገደ የሚገኝ የድሬዳዋ አዲስ መልክ መሆኑን ጠቁመው ሚትስቡሺ ለትሬዲንግ ኢንቨስትመንት የሚረዳውን ጥናት እንዲያደርግና በቢዝነሱ እንዲሰማራ ኮርፖሬሽናቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ሚትስቡሺ ኩባንያ ተቀማጭነቱን በጃፓን ቶኪዮ ያደረገ በተሽከርካሪ ምርት የሚታወቅና በባንኪንግ፤ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፤ በኬሚካል ኢንዱስትሪ እና በሌሎችም ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች የተሰማራና ከ80 ሺ በላይ ሰራተኞች ያሉት አለም አቀፍ ግዙፍ ተቋም ነው።

Mitsubishi expressed his desire to engage in trading investment in Dire Dawa Free Trade Zone.

The well-known international car manufacturer, Mitsubishi, has expressed its desire to the corporation to using the investment options available for trading in Dire Dawa Free Trade Zone.
IPDC’s Investment Promotion and Marketing Deputy CEO Mr. Zemen Junedin, received the company's General Manager, Shigyoshi, and spoke to him at his office.

Among the investment centers managed by IPDC The General manager earlier visited Hawassa, Adama and Bole Limi Industrial Parks and stated that they want to engage in trade-related investments in Dire Dawa Free Trade Zone.

On his part, IPDC’s Deputy CEO Mr. Zemen, pointed out that the Dire Dawa Free Trade Zone is a new face of Diredawa which is currently hosting a large demand for investment in various sectors. And he strongly confirmed that IPDC will support Mitsubishi to do the research that will help it in trading investment and engage in the business.

Mitsubishi has its headquarters in Tokyo, Japan, known for its vehicle manufacturing and also engages in banking, agro processing, chemical industry and other huge investments and has more than 80 thousand employees.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy