• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months, 3 weeks ago
  • 580 Views

"Waste to Wealth"

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እየከወናቸው ከሚገኙ የሪፎርም ተግባራት መካከል "Waste to Wealth" ይገኝበታል።

የዚህ ሪፎርም ዋነኛ አላማ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 13 ግዙፍ የኢንቨስትመንት ማዕከሎች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶችን አዳዲስ ሳይንሳዊ ስልቶችን በመጠቀም መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል ተጨማሪ ገቢን መፍጠር መቻል ነው።

ከዚህ ቀደም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚወጡ ተረፈ ምርቶች አካባቢን በማይጎዳ መልኩ ተለይተው በጥንቃቄ ይወገዱ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ተረፈ ምርቶቹን መልሶ ለሌላ አላማ በመጠቀም ተጨማሪ ገቢን ለመፍጠር ጠንካራ ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድረው ቀደምት እና ግዙፍ በሆነው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተለያዩ አምራች ኩባንያዎች የሚወጡ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶችን በማሰባሰብ እና ሳይንሳዊ ፍተሻ በማድረግ ለብሎኬት ምርት እንዲውሉ ተደርጎ በዛው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሙከራ ምርት እየተመረተ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርትን በመጠቀም በቀን 8000 ብሎኬቶችን ለማምረት እየተሰራ ሲሆን ሙሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ። ለዚህ ስራ መሳካት የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምርትና ስልጠና እንዲሁም የሐዋሳ ተግባዕረ እድ የቴክኒክና ማሰልጠኛ እገዛ እያደረጉ ይገኛል፡፡

ይህ የሪፎርም ተግባር ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ለዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር፤ ለኮንስትራክሽን ዘርፍ ግብዓት የሚሆኑ እንዲሁም ተጨማሪ ገቢዎችን ለማግኘት ትልቅ እድል ይፈጥራል፡፡

ይህ ተረፈ ምርትን ወደ ሀብት የመቀየር የሪፎርም ተግባር በሁሉም ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ሌሎች የኢንቨስትመንት ማዕከላት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

"Waste to Wealth" is one of the reforms being undertaken by Industrial Parks Development Corporation.

The main objective of this reform is to generate additional income by recycling various industrial wastes in the 13 huge investment centers managed by the corporation using scientific methods.

Earlier Waste products from industrial parks were carefully separated and disposed of in eco-friendly way that does not harm the environment. Now, a strong activities are being done to generate additional income by using industrial wastes for other purposes.

In this regard, in the earliest and huge Hawassa Industrial Park managed by the corporation, industrial waste products from various manufacturing companies are collected and scientifically tested in the park to be used for block production.

Production of 8000 blocks per day using industrial wastes is underway at Hawassa Industrial Park and pre operation works are completed. The federal technical and vocational education and training as well as Hawassa Tegbared are supporting the project.

This initial reform process will be strengthened in other investment centers managed by the Corporation.

#Invest_In_Zero_Waiting_Time_Bureaucracy