• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 3 weeks ago
  • 342 Views

የክትባት ማምረቻ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ

ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለሚደረግበት የክትባት ማምረቻ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለሚደረግበትና ሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ለተሰኘው ፕሮጀክት በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የተለያዩ የክትባት አይነቶችን ለማምረት የሚያስችለው የፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያና የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም በዛሬው እለት በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና ፣ ባህልና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ፤ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፤ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ፤ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሀይለሚካኤል፤ የአለም ባንክና ሌጆች ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች፤ የተለያዩ አምባሳደሮች ፤ የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሌሎች የፌደራልና የክልል አመራሮች ታድመዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት ብሎም የዉጪ ምንዛሪን ለማዳን ፕሮጀክቱ ያለዉ አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት የበኩላቸዉን ላበረከቱ አካላት ምስጋና ይገባል ብለዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸዉ ኮርፖሬሽኑ ለሀገር በቀል ኩባንያዎች የሚሰጠዉ ትኩረት ከፍ እያለ መምጣቱን አሳዉቀዉ በተለይም በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን በመገንባት ለአምራቾች አዘጋጅቷል ብለዋል። አክለውም በዘርፉ አቅምና ፍላጎቱ ላላቸዉ ሀገር በቀልና የዉጪ ኩባንያዎች ኮርፖሬሽኑ ከምንግዜዉም በላይ ቀልጣፋና ከረዘመ ቢሮክራሲ የፀዳ አሰራር ዘርግቶ እንደሚቀበል አሳውቀዋል።

አቶ አክሊሉ በመጨረሻም ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ኮርፖሬሽኑ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው ፕሮጀክቱ እውን ሆኖ ስራውን እስኪጀምር ድረስ ኮርፖሬሽኑ ያልተቋረጠ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በዛሬዉ እለት በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የሺልድቫክስ ኢንተርፕራይዝ ፕሮጀክት በመጀመሪያው ዙር ከ70 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ተደርጎበት እ.አ.አ በ2027 ክትባቶችን የማምረት ተግባር እንዲጀምር ዕቅድ መያዙ ተነግሯል።

An investment of more than 70 million dollars is going to be made for the production of vaccine in Kilinto Industrial Park

A project launch program was held today in the KIlinto Industrial Park for the ShieldVax Enterprise, which will be invested more than 70 million dollars, and which enables the production of various types of vaccines,

In FDRE House of Representatives Health, Culture and Sports Standing Committee Leader Mrs. Werkesemu Mamo, Dr. Liya Tadesse, FRDE Minister of Health, IPDC CEO Aklilu Tadesse, Habtamu Hailemichel, Director General of Public Enterprises Holding Adminstration and Management Senior officials of the World Bank and other local and international institutions, Senior officials of the World Bank and other institutions, Ambassadors of different countries, Leaders of the Customs Commission and other federal and regional officials were present at the program.

Speaking at the program, the Minister of Health, Dr. Liya Tadesse, pointed out that the contribution of the project to replace imported products in the country and save foreign currency is significant. And she added that a positive appreciation is a must to those who contributed to the success of this project.

Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse, on his part, informed that the corporation is paying more attention to local companies, especially in the pharmaceutical sector, by building and dedicating Kilinto Industrial Park for manufacturers in the sector. He added that for domestic and foreign companies that do have the capacity and interest in the sector, IPDC is providing Zero Waiting Time Service that is more efficient than ever and free from lengthy bureaucracy.

The ShieldVax Enterprise project, which was laid the foundation stone in Kilinto Industrial Park today and which more than 70 million dollars will be invested in the first phase, plans to start manufacturing vaccines in 2027.