• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 1 week ago
  • 324 Views

የዋና ስራ አስፈፃሚው ወቅታዊ መልዕክት

"ኢትዮጵያ የትዉልዱን የባህር በር ጥያቄ መመለስ በቻለችበት ማግስት ኢንቨስት ለማድረግ ውል የፈረሙ ኩባንያዎች የተፈጠረላቸው እድል ሌሎችን ለኢንቨስትመንት የሚያነሳሳ ነው" - አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኢትዮጵያ የትዉልዱን የባህር በር ጥያቄ  መመለስ በቻለችበት ማግስት ኢንቨስት ለማድረግ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል የፈረሙ ኩባንያዎች የተፈጠረላቸው እድል ሌሎችን ለኢንቨስትመንት የሚያነሳሳ መሆኑን ገለፁ።

አቶ አክሊሉ ታደሰ ይህን የገለፁት ከ 11 ሀገር በቀልና የውጪ ኩባንያዎች ጋር በተለያዩ የኢንቨስትመንት ማዕከሎች በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ከኮርፖሬሽኑ ጋር የውል ስምምነት በፈረሙበት ወቅት ነው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው በውል ስምምነት ስነ-ስርዓቱ ወቅት  ኢትዮጵያ የባህር በር ማግኘቷ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ያለ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲጨምር እንደሚያስችል አንስተዋል።

በሌላ በኩልም አምራች ባለሀብቶችና ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን ለውጪ ሀገር ገበያ እንዲያቀርቡ ብሎም ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚረዱ ግብዓቶችን በፍጥነት እንዲደርሳቸው የሚፈጥረው እድል ግዙፍ መሆኑና ለወጪ ገቢ ንግድ ፍሰት ያለው አስተዋፆ ጉልህ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ አክሊሉ አክለውም በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባው መቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ ቀድመው ከነበሩ ኩባንያዎች በተጨማሪ ሶስት አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ያስተናግዳል ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው 5 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚሰማሩ፤ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡና ከአምስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣት ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥሩ ኢንቨስትመንቶች በትናንትናው እለት መፈረማቸው የሚታወስ ነው።