• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 10 months, 2 weeks ago
  • 527 Views

በፓርኮች የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ

በፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ የባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

በኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እና የልማት ባንክ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል።

የስራ ኃላፊዎቹ በጉብኝታቸው በፓርኮች ኢንቨስት ያደረጉ ባለሀብቶችን እና በአዳዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚያጋጥማቸውን የፋይናንስ እና የግብዓት እጥረት ከሚመለከታቸው ጋር በመነጋገር ለመፍታትና በፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት በማየት ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽንና ማኔጅመንት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሚል ኢብራሂም ገልፀዋል።

አቶ ካሚል በተጨማሪም በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለመስራት ስምምነት የተፈራረሙ ባለሀብቶች በቶሎ ወደስራ እንዲገቡ ለማድረግና በዘርፉ ተሳታፊ የሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ የመስራት ባህልን በማዳበር በተለይም የግብዓትና የፋይናንስ ችግሮችን ለመቅረፍና ተግዳሮቶችን በአጭር ጊዜ ለመፍታት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ተመልክተው የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል።

በጉብኝቱ የተሳተፉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው በፓርኮቹ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ገልፀው ወደ ስራ የሚገቡ ባለሀብቶች በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ ለማስቻል በተቋማቱ በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት አስፈላጊውን መስፈርት አሟልተው የሚመጡ ከሆነ ቅድሚያ ሰጥተው ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓሬሽን በፓርኮች ያለውን የስራ እንቅስቃሴ የተሻለ ለማድረግና በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚያስችል የኢንቨስተሮችና የባለድርሻ አካላት የውይይት ፎረም ማካሄዱ ይታወሳል ።