• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 3 weeks ago
  • 231 Views

አሁን

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የቢራ ገብስ ብቅል ማቀነባበር ላይ ለተሰማሩ የውጪ ኩባንያዎች የቢራ ገብስ የሚያቀርቡ አርሶ አደሮችን በምዕራብ አርሲ ዞን በሚገኙት በሻሸመኔ ወረዳ ሁርሳ ቀበሌ እና ቆሬ ወረዳ ዶዳ ደዩ ቀበሌ እየጎበኙ ነው።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ከኮርፖሬሽኑ ስራ አመራር ጋር እያደረጉ ባሉት ጉብኝት በቦሌ ለሚ  ኢንዱስትሪ ፓርክ  ለሚገኘው አለም አቀፉ የሱፍ ሌት የቢራ ብቅል አምራች ኩባንያ የሚሆን ከ60 ሺህ ቶን በላይ ገብስ ለኩባንያው በማቅረብ ኢትዮጵያ ከውጪ ታስገባው የነበረውን የብቅል ምርት ሙሉ በሙሉ በስቀረትና ለውጪ ምንዛሪ ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ ዶላር ማስቀረት ከቻሉ አርሶ አደሮች መካከል የሆኑትን አርሶ አደሮች ማሳቸው ላይ በመገኘት የተመለከቱ ሲሆን ከአርሶ አደሮቹ ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።