• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 8 months, 2 weeks ago
  • 291 Views

የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢና የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ መልዕክት

የኮርፖሬሽኑ የሪፎርም ስራዎች የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ተሳትፎ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል” አቶ ገብረ መስቀል ጫላ

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ተሳትፎ ለማሳደግ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን  የተተገበሩት የሪፎርም ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻላቸውን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስቴርና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ ገለጹ፡፡

ሚኒስቴሩ  ይህን የገለጹት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ተግዳሮቶችን በትብብርና በቅንጅት በመቅረፍ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለመጨመር ያለመ የኢንቨስተሮችና የባለድርሻ አካላት የጋራ ፎረም  በተካሄደበት መድረክ ላይ ነው፡፡

የቦርድ ሰብሳቢው ኢንዱስትሪ ፓርኮቹ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማስገኘት አላማ አድርገው ቢቋቋሙም የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች አቅሙና የመስራት ፍላጎት እስካላቸው ድረስ ገብተው እንዲሰሩ መደረጉ በርካታ ለውጦች እንዲመዘገቡ ማድረግ መቻሉንና ይሕም የሚበረታታና በቀጣይም በትኩረት መሰራት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በፓርኮችና በኢንቨስትመንት ማዕከሎች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሳትፈው እንከን እየገጠማቸው የሚገኙ ባለሀብቶችና አምራች ኩባንያዎችን ለመደገፍ እንዲሁም አዲስ ኢንቨስትመንት እያሰቡ የሚገኙ ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠርላቸው በማለም እየተሰራበት ያለውና እድገት ያሳየው የተቋማት የቅንጅት አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ገብረመስቀል አሳስበዋል።