• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months ago
  • 288 Views

የዋና ስራ አስፈፃሚው መልዕክት

"ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ያደረገው ሪፎርም ሙሉ ለሙሉ ውጤታማ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው" - አክሊሉ ታደሰ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ እያደረገው ላለው ግዙፍ ተቋማዊ ሪፎርም ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት ኮርፖሬሽኑ በአይነቱና በግዝፈቱ የመጀመሪያ የሆነውን የኢንቨስተሮችና የባለድርሻ አካላት የጋራ ፎረም በአዲስ አበባ ባካሄደበት ወቅት ነው። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኮርፖሬሽኑ የያዘውን ግዙፍ ሀገራዊ ዓላማ በአፋጣኝ ማሳካት እንዲችል የባለድርሻ አካላት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ፎረሙ መዘጋጀቱን አሳውቀዋል። 

የባለድርሻ አካላት ከሌላው ግዜ በተሻለ መልኩ ተቀራርቦ መስራት በኢንቨስትመንት ላይ ተሰማርተው በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶችና ኩባንያዎች የሚገጥሟቸውን እክሎች በአፋጣኝ ለመፍታት ብሎም ለአዳዲስ ኢንቨስተሮችና ኩባንያዎች ምቹ የኢንቨስትመንት ከባቢ ለመፍጠር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አቶ አክሊሉ ጨምረው ገልፀዋል። 

ኮርፖሬሽኑ በአቅሙ መፍታት የሚችላቸውን የኢንቨስተሮች ቅሬታ በአፋጣኝ ለመፍታት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር ከምንግዜውም በላይ በቅንጅት ለመስራት ዝግጅቱ ከፍ ያለ መሆኑን በመልዕክታቸው የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን መሰል ፎረሞች ቢያንስ በዓመት ሁለት ግዜ በቋሚነት ለማዘጋጀት እቅድ እንደተያዘ አሳውቀዋል። 

በኮርፖሬሽኑ አዘጋጅነት በካሄደው የባለድርሻ አካላትና የኢንቨስተሮች ፎረም ከኢንቨስትመንትና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተገናኙ የውይይት ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

"The role of stakeholders is crucial for the reform implemented by the corporation to be fully effective" IPDC CEO

Aklilu Tadese, CEO of Industrial Parks Development Corporation, stated that the role of stakeholders is crucial to the effectiveness of the massive institutional reform that the corporation is implementing.

The CEO stated this when the corporation held the first joint forum of investors and stakeholders in Addis Ababa.

In his message at the opening of the forum, the CEO announced that the forum has been prepared because the role of the stakeholders is crucial so that the corporation can achieve the huge national goal expected as a county as soon as possible.

Mr. Aklilu added that working in cooperation with the stakeholders in a positive way than before will create a great opportunity to quickly solve the problems faced by investors and companies in industrial parks and to create a favorable investment environment for new investors and companies.

The CEO stated in his message that the corporation is more ready than ever to solve the complaints of  investors as soon as possible and to work in coordination with the stakeholders. He informed that there is a plan to organize such forums at least twice a year.

Discussion documents related to investment and stakeholders were presented and discussed at the stakeholder and investor forum organized by IPDC.