• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months ago
  • 260 Views

ከ10 ቢሊየን ሩብል በላይ ካፒታል ያለው የሩሲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢንዱስትሪ ፓርኮች

ተቀማጭነቱን በሩሲያ ፌደሬሽን ኦሪዮል ግዛት ያደረገ ግዙፍ የአግሮ ፕሮሰሲንግ ግሩፕ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ሊያመርት ነው

17 ግዙፍ አምራች ኩባንያዎችን የያዘ የሩሲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ መወሰኑን ገልጿል።

ከ10 ቢሊየን ሩፕል በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገበና 17 ግዙፍ የሩሲያ አምራች ኩባያዎችን ያቀፈ አግሮ ግሩፕ ኢንቨስት የተሰኘ የሩሲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት ለማድረግ መወሰኑን ገልጿል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የኢንቨስትመንት ግሩፑን ዳይሬክተር ካትኮቭ ዴኒስ እና የስራ ባልደረቦቻቸውን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንቨስትመንት ግሩፑ የደረሰበት ውሳኔ ትክክለኛ እና ጊዜውን የዋጀ መሆኑን አንስተው ኮርፖሬሽኑ በተለይም ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ያዘጋጀውን የኢንቨስትመንት አማራጮች፤ ማበረታቻዎች፤ መንግስት ዘርፉን ለማበረታታት ባለፉት ዓመታት ያዘጋጃቸውን አስቻይ ፖሊሲዎች እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎችን በዝርዝር ለተወካዮቹ አስረድተዋል። በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ ኢንቨስትመንቱ እውን እንዲሆን ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የኢንቨስትመንት ግሩፑ ዳይሬክተር ካትኮቭ ዴኒስ ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለፃ ምስጋናቸውን አቅርበው በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ የተሰማራው ግሩፕ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት ለማድረግ መወሰኑን አድንቀው የቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናቶችን እና መረጃዎችን እያጠናቀረ መሆኑን አሳውቀዋል።

በነበረው ውይይት በሩሲያ የሚገኘውን ከፍተኛ የጋርመንትና ቴክስታይል ገበያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራች ኩባንያዎች መጠቀም እንዲችሉም ውይይት ተደርጓል።

አግሮ ግሩፕ ኢንቨስት የተሰኘው የሩሲያ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተቀማጭነቱን በሩሲያ ፌደሬሽን ኦሪዮል ግዛት ያደረገ ሲሆን 17 አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመያዝ በ100 ሺ ሄክታር መሬት ላይ ለኢንዱስትሪ ግብዓት መኖ የሚዉሉ ዘርፈ ብዙ የግብርና ምርቶችን እያመረተ ይገኛል።

The Russian Investment Group, which consists of 17 large manufacturing companies, has announced its decision to invest in industrial parks.

A Russian investment group named AGROGROUPINVEST, which consists of 17 huge Russian manufacturers and has an investment capital of more than 10 billion rubles, has announced its decision to invest in industrial parks.

Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse, received the Director of the Investment Group, and his advisor in his office.

The CEO emphasized that the investment group's decision was right and timely, and He explained to the representatives the investment options that IPDC has prepared, especially for the agro-processing sector, incentives, and enabling policies prepared by the government as well as various incentives.

He also assured that the corporation will provide continuous support to make the investment a reality.

The Director of the investment group, Katkov Denis, thanked for the welcome and presentation and stated that the group engaged in the agro-processing sector has decided to invest in industrial parks and informed that it is compiling pre-investment studies and information.

In the discussion, it was also discussed in a way that manufacturing companies located in industrial parks can use the huge garment and textile market in Russia.

AGROGROUPINVEST, a Russian investment group in Oryol region of the Russian Federation and owns 17 manufacturing industries on 100,000 hectares of land, acquiring a wide range of agricultural products for industry and animal feed.