• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 1 week ago
  • 302 Views

የኢትዮ-ብራዚል ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም

"ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከብራዚል ጋር ያላትን የቀደመ ግንኙነት በኢንቨስትመንት ለማጠናከር አይነተኛ ሚና ይጫወታል" አክሊሉ ታደሰ 

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የተሳተፈበትና በብራዚል ኤምባሲ አማካኝነት የተዘጋጀው የኢትዮ-ብራዚል የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ተካሄደ። 

በፎረሙ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ባደረጉት ንግግር የብራዚል ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። 

ዋና ስራ አስፈፃሚው በመልዕክታቸው ኮርፖሬሽኑ በተለይም ለውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በሰጠው ልዩ ትኩረት የአሰራር ሪፎርሞችን ተግባራዊ በማድረግና ባጠረ ቢሮክራሲ በዘመናዊ መንገድ አገልግሎት በመስጠት ኢንቨስተሮችን እያስተናገደ እንደሚገኝ አሳውቀዋል። 

በቅርቡ ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከብራዚል ጋር ያላትን የቀደመ ግንኙነት ይበልጡኑ በኢንቨስትመንት በማሳደግ በኩል የሚኖረው ሚና ጉልህ መሆኑን ያስታወሱት አቶ አክሊሉ ለዚህም የብራዚል አምራች ኩባንያዎችና ባለሀብቶች በተለይም በማኑፋክቸሪንግ እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ በኢንዱስትሪ ፓርኮችና በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል። 

የኢትዮ-ብራዚል ትሬድና ኢንቨስትመንት ፎረም በዛሬው እለት በአዲስአበባ በተለያዩ ሁነቶች የተካሄደ ሲሆን በዚሁ ፎረም ላይ የተሳተፉ የብራዚል ከፍተኛ ባለስልጣናትና ልዑኮች በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ይፋዉ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። 

'Ethiopia's joining BRICS will play an important role in strengthening its relationship with Brazil through investment' IPDC CEO 

The Ethio-Brazil Trade and Investment Forum organized by the Brazilian Embassy was held with the participation of the Industrial Parks Development Corporation. 

In his speech at the forum, IPDC CEO, Aklilu Tadesse, called on Brazilian investors to invest in industrial parks and the Free Trade Zone of Dire Dawa. 

In his message, the CEO informed that the corporation is dealing with investors by implementing operational reforms and providing services in a modern way with a special focus on foreign direct investment. 

Mr. Aklilu reminded that Ethiopia's recent accession to BRICS will play a significant role in increasing its previous relationship with Brazil through investment. He therefore called on Brazilian manufacturing companies and investors to engage in investment, especially in the manufacturing and agro-processing sectors, in industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone. 

The Ethio-Brazilian Trade and Investment Forum was held today in Addis Ababa with various events, and it is expected that the Brazilian high officials and delegates who participated in the forum will pay an official visit in Bole Lemi Industrial Park.