• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 1 week ago
  • 290 Views

አዲሱ የኮርፖሬሽኑ ተቋማዊ መዋቅር

የኮርፖሬሽኑን ሰራተኞች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ተቋማዊ መዋቅር ለቀጣይ 5 ዓመታት መዘርጋቱ ተገለፀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለቀጣይ አምስት አመታት የሚገለገልበትን ተቋማዊ መዋቅር ለሰራተኞቹ ይፋ አድርጓል።

ይህንን መዋቅር ለሰራተኞች ይፋ ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሰይፉ ናቸው።

አቶ አለማየሁ በመድረኩ እንደገለፁት የኮርፖሬሽኑን ሰራተኞች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ተቋማዊ መዋቅር ለቀጣይ 5 አመታት መዘርጋቱንና ይህም ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነታቸውን በመጨመር ተቋሙ የያዘውን ሀገራዊ አላማ በውጤት ለማሳካት ትልቅ ሚና እንደሚኖረው አሳውቀዋል።

በመድረኩ የመዋቅር አዘገጃጀትና የምደባ አተገባበር ላይ ዝርዝር ሰነድ ለራተኞች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በውይይቱ መሰረትም ቀጣይ የመዋቅር ትግበራ እንደሚከናወን ተገልጿል ።