• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 9 months, 1 week ago
  • 292 Views

ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል ከተፈራረሙ ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ጋር የተደረገ ውይይት

"ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል ተፈራርመው ወደ ስራ ያልገቡ ኩባንያዎችና ባለሀብቶች በአፋጣኝ ወደ ስራ መግባት አለባቸው" - አክሊሉ ታደሰ

ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል ተፈራርመው ኮንትራት የወሰዱ ሀገር በቀልና የውጪ ኩባንያዎች በአፋጣኝ ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ገለፁ።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ይህን የገለፁት ባለፈው አንድ አመት ውስጥ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል ከፈፀሙ ኩባንያዎችና ባለሀብቶች ጋር በተደረገ የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

ውል ተፈራርመው የማምረቻ ሼድና የለማ መሬት ወስደው ግንባታና ማሽን ተከላ የጀመሩትን በመደገፍ ወደ ማምረት ሂደት እስኪገቡ ድረስ ኮርፖሬሽኑ ያልተቋረጠ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አክሊሉ በሙሉ አቅም ወደ ምርት ሂደት የገቡትን ደግሞ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተለያዩ አለም አቀፍ ገበያዎችን በማፈላለግ ጭምር ድጋፍ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል።

የዉይይት መድረኩ ባለፈው አንድ አመት ከኮርፖሬሽኑ ጋር ውል ፈርመው በተለያየ የኢንቨስትመንት ትግበራ ደረጃ ላይ ካሉ ኩባንያዎች እና ባለሀብቶች ጋር የተደረገ ሲሆን በመድረኩም የኮርፖሬሽኑ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎችን እና የኢንቨስትመንት ፍሰት መረጃዎች በዝርዝር ቀርበው ውይይት የተደርገባቸዉ ሲሆን ባለሀብቶችና ኩባንያዎችም ሀሳባቸውን አካፍለዋል።

የዉይይት መድረኩ ዋነኛ አላማ ከኮርፖሬሽኑ ጋር ዉል ተዋዉለዉ በአጭር ጊዜ ወደ ግንባታና የምርት ሂደት የገቡትን ለማበረታታትና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተግባር ያልገቡትን በመለየት ለመደገፍ ያለመ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

በቀጣይም መሰል መድረኮች የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላትና አጠቃላይ ኢንቬስተሮች በሚገኙበት እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

Companies and investors who have signed contracts with IPDC should start pre and After Investment Operations immediately" – IPDC CEO Aklilu Tadesse

Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse said that local and foreign companies that have signed contracts with the corporation should start pre and post investment operations immediately.

The CEO disclosed this in a discussion with companies and investors who signed contracts with the corporation in the last one year.

Mr. Aklilu pointed out that IPDC is providing uninterrupted support to those who have signed a contract, taken production sheds and service land, started construction and installed machinery until they start full operation.

He added that, investors who have signed a contract with the corporation and are at different stages of investment implementation needs to be effective and start operation as soon as possible.

In the forum, the corporation's current activities and investment flow data were presented in detail and discussed. Investors and companies also have shared their thoughts.

It has been stated that similar forums will be held where various stakeholders and general investors will be present.