ለፈረንሳይ አምራች ኩባንያና ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ቀረቡ
ከፈረንሳይ ሀገር ለተውጣጡና በኢትዮጵያ በዘርፈ ብዙ ኢንቨስትመንቶች ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ላሳዩ አምራች ኩባንያዎችና ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲሁም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ቀርበውላቸዋል።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን አማራጮቹ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ኮርፖሬሽናቸው በሚያስተዳድራቸው የኢንቨስትመንት ማዕከሎች በርካታ አዋጭና ምቹ አማራጮች መኖራቸውን ጠቁመው በዋናነትም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የንግድና የሎጂስቲክ ዘርፍ እንዲሁም በባህርዳርና ጂማና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፍ ያልተነኩ እምቅ እድሎች እንዳሉ አሳውቀዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአግሮፕሮሰሲግ ዘርፍ የተሰማራው ግዙፉ የፈረንሳይ የብቅል አምራች ኩባንያ ሱፍሌ ኢትዮጵያ በውጪ ምንዛሪ ታስገባው የነበረውን ምርት ሙሉ በሙሉ በማስቀረት በኩል ሚናው ከፍተኛ እንደሆነና ከ50 ሺ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች የገበያ ትስስር መፍጠሩን በማስታወስ ኮርፖሬሽኑ በፓርኮቹ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሰማራት ፍላጎቱ ላላቸው አዳዲስ ኩባንያዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በመድረኩ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ፤ የተገነቡና ለአምራቾች የቀረቡ አስቻይ መሰረተ ልማቶችን ፤ ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችንና ማበረታቻዎችን እንዲሁም መሰል ዝርዝር ኢንቨስትመንት ተኮር ጉዳዮችን የተመለከተ ዝርዝር ሰነድ ቀርቦ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።
Favorable investment options in industrial parks were presented to French manufacturing companies and investors
Manufacturing companies and investors from France who are engaged in multi-sector investments have been offered convenient investment options in industrial parks and Dire Dawa Free Trade Zone.
Industrial Parks Development Corporation CEO Aklilu Tadesse and Investment Commission Deputy Commissioner Temesgen Tilahun briefly explained the options.
IPDC CEO, Aklilu Tadesse, pointed out that there are many viable and convenient options in the investment centers managed by the corporation, and he informed that there are potential opportunities especially in Dire Dawa Free Trade Zone in wide areas of trade, logistics and Import/Export also in the sector of agro processing in other parks.
The CEO added that the huge French malt company established in Ethiopia, Souffle Ethiopia, played a significant role in import substitution and created a market linkage for more than 50 thousand farmers. He assured that IPDC will provide full support to new companies that are interested.
Finally, Investment options available in industrial parks; Enabling infrastructure developed and provided to manufacturers; favorable investment policies and incentives and similar investment-oriented issues has been presented and explained.