የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳህረላ አብዱላሂ ተፈራርመዋል።
የመግባቢያ ስምምነቱ ኮርፖሬሽኑ ሲጠቀምበት የቆየውን የኢነርጂ አጠቃቀም ፍጆታ በማሻሻል ካለበት የፍጆታ ደረጃ በ10 በመቶ ለመቀነስ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል። ለዚህም ፈጣንና ዘመናዊ የኢነርጂ አጠቃቀም ማሻሻያ ዘዴዎችን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ ለስምምነቱ ተግባራዊነት ከሁለቱም ተቋማት የተወጣጣ የኢነርጂ ማኔጅመንት ዩኒት የሚቋቋም ሲሆን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለ ኢነርጂን ኦዲት ማድረግና አጠቃቀምን ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተገልጿል።
Industrial Parks Development Corporation signed a memorandum of understanding with the Petroleum and Energy Authority
The MoU was signed by IPDC CEO, Aklilu Tadesse, and Sahrela Abdullahi, Director General of Petroleum and Energy Authority.
It has been pointed out that the memorandum of understanding aims to reduce the current energy consumption level of IPDC by 10 % by improving the energy consumption that the corporation has been using. For this, it has been stated that fast and modern methods of improving energy use will be implemented jointly with the authority.
In addition to this, for the implementation of the agreement, an energy management unit will be established from both institutions, and it will focus on auditing and improving the use of energy in industrial parks.