በፋርማሲዩቲካል ማኑፋክቸሪንግ ላይ የተሰማሩ የህንድ ባለሀብቶች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማምረት ያላቸውን ፍላጎት ገለፁ
ባለሀብቶቹ የኢንቨስትመንት ፍላጎታቸውን የገለፁት የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ መሰረተ ልማት ፤ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንዲሁም የኢንቨስትመንት ፖሊሲዎችና ማበረታቻዎችን የተመለከቱ ዝርዝር መረጃዎች ከቀረቡላቸውና ፓርኩን ከጎበኙ በኋላ ነው።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘመን ጁነዲን ባለሀብቶቹን አነጋግረዋል።
ምክትል ስራ አስፈፃሚው በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው ኢትዮጵያ ለፋርማሲዩቲካል ዘርፍ በሰጠችው ግዙፍ ሀገራዊ ትኩረት ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን በተለየ ሁኔታ ለዘርፉ ማመቻቸቷን ገልፀው ፤ የህንድ ባለሀብቶች ተሳትፎም በየ ጊዜው እያደገ መምጣቱን አንስተዋል። በተጨማሪም ኮርፖሬሽናቸው በዘርፉ መሰማራት ለሚፈልጉ አለም አቀፍና የአገር ዉስጥ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት ያደረጉት የህንድ ባለሀብቶች በፓርኩ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችንና የአገልግሎት አሰጣጥን ተመልክተው ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በፓርኩ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት አሳይተዋል።
ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ279 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ እና ለፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ታስቦ የተገነባ ሲሆን አለም አቀፍና ሀገር በቀል የዘርፉን ባለሀብቶችና ኩባንያዎች እያስተናገደ ይገኛል።
Indian investors engaged in pharmaceutical manufacturing expressed their interest in manufacturing at Kilinto Industrial Park.
The investors expressed their desire to invest in the Park After their visit in the compound. And they are provided with detailed information about the services, investment policies and incentives as well as the State of The Art Infrastructures of the park.
IPDC’s Investment Promotion and Marketing Deputy CEO, M.r Zemen Junedin, spoke to the investors.
M.r Zemen In his welcome message, explained that Ethiopia has specially facilitated Kilinto Industrial Park for the pharmaceutical sector due to the huge national attention it has given to the sector. He mentioned that the participation of Indian investors is also growing and confirmed that IPDC will provide all necessary support to international and local investors who want to engage in the sector.
The Indian investors who visited Kilinto Industrial Park expressed their happiness after seeing the infrastructure and service delivery in the park and showed interest in investing in the park.
Kilinto Industrial Park is located in Addis Ababa in 279 hectares of land and was built for the pharmaceutical sector and is hosting international and local investors and companies in the sector.