• +251118722266
  • Striving for eco industrial park
logo
  • by admin
  • 0Comments
  • 1 year, 1 month ago
  • 951 Views

የኮርፖሬሽኑና የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ስምምነት

"በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት መሟላት የቀጠናውን አቅም ያሳድገዋል" - አክሊሉ ታደሰ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የሎጀስቲክስ አገልግሎት ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) ተፈራርመዋል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና በሙሉ አቅሙ ስራ እንዲጀምር ከሚያስችሉ ጉዳዮች መካከል የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት አንዱ መሆኑን ጠቁመው የዚህ አገልግሎት በነፃ ንግድ ቀጠናው መቀላጠፍ ቀጠናው ያለውን አቅም በእጅጉ እንደሚያሳድግ ገልፀዋል።

የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) በበኩላቸው ተቋማቸው በነፃ ንግድ ቀጠናው አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑንና ከኮርፖሬሽኑ ጋር ሀገራዊ ፋይዳው ጉልህ የሆነውን ነፃ ንግድ ቀጠና አገልግሎት ለማቀላጠፍ በቅንጅት ለመስራት ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳውቀዋል።

ስምምነቱ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና አስፈላጊውንና ዘርፈ ብዙ የሎጀስቲክስ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና የሚኖሩ አምራቾች፤ አስመጪ እና ላኪዎች እንዲሁም በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች የሚገኙ ባለሀብቶች የሚያስፈልጓቸውን የሎጀስቲክስ አገልግሎቶች በተመደቡ ሰራተኞችና ኃላፊዎች በነፃ ንግድ ቀጠናው እንዲያገኙ እንደሚያስችል በመድረኩ ተገልጿል።

በተጨማሪም ስምምነቱ አላስፈላጊ ቢሮክራሲን በማስቀረት፤ ጊዜን በመቆጠብና ከዚህ በፊት የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን የገቢ ወጪ ንግድና አገልግሎትን በማሳለጥ የሀገሪቷን ኢኮኖሚ አንድ ደረጃ ከፍ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

'Transportation and logistics services in Dire Dawa Free Trade Zone will increase the capacity of the Zone' - Aklilu Tadesse

Industrial Parks Development Corporation signed a Logistics service agreement with Ethiopian Shipping and Logistics service.

The agreement was signed by Industrial Parks Development Corporation CEO, Aklilu Tadesse, and CEO of Ethiopian Shipping and Logistics service Beriso Amelo (Dr.).

Speaking during the signing ceremony, IPDC CEO, Aklilu Tadesse, pointed out that transport and logistics services are one of the factors that will enable Dire Dawa Free Trade Zone to start working at its full Capacity. He added that the facilitation of this service in the free trade zone will greatly increase the potential of the zone.

Ethiopian Shipping and Logistics service CEO, Beriso Amelo (Dr.) said that his institution is ready to provide the necessary services in the free trade zone and that they are committed to working together with the corporation to streamline the service of the free trade zone, which has significant national importance.

It is stated that the agreement will enable Ethiopian Shipping and Logistics service to provide the necessary and multifaceted logistics services in Dire Dawa Free Trade Zone.

It has been informed in the ceremony that importers and exporters as well as investors in various trade and investment sectors will be able to get the logistics services they need through designated employees and officials of Ethiopian Shipping and Logistics service in the zone.

In addition, the agreement will avoid unnecessary bureaucracy; and it is expected that by saving time and consolidating previously started collaborations, Dire Dawa Free Trade Zone will raise the level of revenue, expenditure, trade and services.