ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የኮርፖሬሽኑ የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት ግምገማ ተጠናቋል።
በግምገማ መድረኩ ዘርፎች ዝርዝር የእቅድ ሪፖርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፤ ጠቃሚ ግብዓቶችም የተገኙበት ሆኗል።
ለሶስት ቀናት በቆየው የግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ ትኩረት በሚሹና የተሻለ ውጤት ሊመዘገብባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።
በዋና ስራ አስፈፃሚ ከተቀመጡ አቅጣጫዎች መካከል
ገቢ ማሰባሰብ ላይ በከፍተኛ ትኩረት መሰራት እንደሚገባ፤
ዲጂታላይዜሽንን በተመለከተ ተቋሙ ለጀመረው ስርነቀል ሪፎርም ውጤታማነት የጀርባ አጥንት በመሆኑ የተጀመሩ ስራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ሲስተም ቤዝ የሆነ ወረቀት አልባ የስራ ከባቢ ለመፍጠር እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው እንዲቀጥሉ፤
በየደረጃው የሚገኙ የኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች፤ አማካሪዎችና ባለሙያዎች በእቅዳቸው መሰረት የተቆጠሩ ስራዎችን ቆጥረው እንዲረከቡና እንዲያስረክቡ፤ የሰው ሀይል ልማትን በተመለከተ ለተለያዩ ተቋማዊ ማበረታቻዎች ማን ምን ላይ ይገኛል የሚለውን መመዘን የሚያስችል ውጤት ተኮር የምዘና ስርዓት በማዘጋጀት በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲገባ፤
ተቋማዊ መዋቅር ላይ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ተግባራዊ እንዲሆኑና በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት ተፈፃሚ እንዲሆኑ እንደሚደረግና ለዚህም በየደረጃው አስፈላጊ የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራ፤
ወጪን በመቀነስ ገቢን የማሳደግ መርህ በተቋሙ ባህል አድርጎ የማስረፅ ኃላፊነት የሁሉም መሆኑን መቀበልና ለዚህም አዳዲስ ወጪ ቆጣቢ አሰራሮችና እይታዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ፤
የተጀመሩ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎች አሁን ላይ ከደረሱበት ደረጃ ይበልጥ ውጤታማ ለመሆን ፍጥነትና ጥራትን አዋህደን በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ፤
የፓርኮቻችን ሰላምና ደህንነት ከየትኛውም ጉዳይ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑና በኮርፖሬሽን ደረጃ ተግባራዊ የተደረጉና በሁሉም ፓርኮችና ነፃ ንግድ ቀጠና ተግባራዊ የተደረገው የብራንዲንግ እሳቤ ተጠናክሮ ተግባራዊ ለደረግ እንደሚገባ፤ … ዋና ዋናዎቹ ናቸው።